top of page

ነሀሴ 1፣2016 - በዋግህምራ ዞን በዘንድሮ የክረምት ወቅት ዝናብ ቢያገኝም በአንዳንድ አካባቢዎች ከፍተኛ ዝናብ በማጋጠሙ ለእንስሳት ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል

ባለፉት ሶስት ዓመታት ዝናብ ጠብ ባለማለቱ እና በድርቅ ሲፈተን የቆየው የዋግህምራ ዞን በዘንድሮ የክረምት ወቅት ዝናብ ቢያገኝም በአንዳንድ የዞኑ አካባቢዎች ከፍተኛ ዝናብ በማጋጠሙ ምክንያት ለእንስሳት ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል፡፡


የነዋሪዎች ቤትም በላያቸው ላይ መፍረሱን ሰምተናል፡፡


በዞኑ በአንዳንድ ወረዳዎች ከፍተኛ ዝናብ መዝነቡን ተከትሎ ጎርፍ እንደተከሰተ የተነገረ ሲሆን በዚህም 80 የሚሆኑ እንሰሳት በጎርፍ መወሰዳቸውን ሸገር ሰምቷል፡፡


ከዚህ በተጨማሪም በርከት ያለ ሄክታር ላይ የበቀሉ #ሰብሎች ላይ ጉዳት ማድረሱን የተናገሩት የዞኑ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ምህረት መላኩ ይህ ደግሞ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ዞንኑ ያሰጋዋል ብለዋል፡፡


ቀደም ሲል ክረምቶችን ሲቋቋሙ የቆዩ ተራሮች እና የነበሩ ተፋሰሶች ዞኑ አጋጥሞት በቆየው #የሰላም _እጦት ድርቅ እና ሌላ ሌላውም ችግር አሁን ላይ ከፍተኛ ዝናብን የመቋቋም አቅም አሳጥቶታል ብለዋል ሃላፊው፡፡


ላለፉት ሶስት አመታት ዝናብ ጠብ ያላለበት የዋግህምራ ዞን በረሀብ በተለያዩ ወረርሽኞች እና በሰላም እጦት ሲፈተን መቆየቱ ይታወቃል፡፡


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page