ታሪክን የኋሊት - ሚያዝያ 2 2017 -በዓለም ታሪክ ከፍተኛና እስካሁን ተወዳዳሪ ያልተገኘለት እሳተ ገሞራ
- sheger1021fm
- Apr 10
- 2 min read
በዓለም ታሪክ ከፍተኛና እስካሁን ተወዳዳሪ ያልተገኘለት እሳተ ገሞራ በኢንዶኔዥያ የፈነዳው በ1807 ዓ.ም በዛሬው ቀን ነበር፡፡
የኢንዶኖዥያ ግዛት በሆነችው፣ ሱምባዊ ደሴት በሚገኘው የታምቦራ ተራራ የፈነዳው እሳተ ገሞራ፣ ሃያል ስለነበረ አካባቢውን የሚገኘውን ሁሉ ድንጋይ መሬት ጭምር አቅልጧል፡፡
የፍንዳታው ድምፅና እንቅጥቃጤ፣ በ2 ሺህ 600 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው፣ የሱማርታ ደሴት ተሰምቷል፡፡
ከ300 ኪሎ ሜትር በላይ፣ ለሚርቁት ታይላንድና ላኦስ እንቅጥቃጤው ደርሷቸዋል፡፡
ከቀኑ 7 ሰዓት የተከሰተው ፍንዳታ ድምፅ እስከ ምሽቱ ቆይቷል፡፡
ፍንዳታው ያቀለጣቸው ግዑዝ ነገሮች አመድ በአካባቢ ባሉ ሌሎች ሀገሮች ሲናኝ ከረመ፡፡
100 ኪዩቢክ ኮሎ ሜትር መሬት፣ በፍንዳታው ወድሟል ወይም ሰምጧል፡፡
4 ሺህ 300 ሜትር ከፍታ ያለው የታምቦራ ተራራ ቁጥሮቹና አፈሩ ቀልጠው ወደ 2 ሺህ 850 ሜትር አንሶ ተገኝቷል፡፡

ቋጥኞቹ ቀልጠው የግለት ፍሳሻቸው ምድሩን ስላሰጠመው መሬት የት እንደነበረ ምልክቱ ጠፋ፡፡
በደቂቃዎች ውስጥ በአካባቢው የነበሩት መንደሮችና ነፍስ ያላቸው ሁሉ ሞቱ፡፡
ጫካዎች ሰርገው የተረፉት በውቅያኖሱ ተንሳፈፉ፡፡
የተለያዩ ዝርያ ያላቸው አዕዋፋት ጠፋ፡፡
በዚያ አስደንጋጭ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ የሞቱት የሰዎች ቁጥር በትክክል ለማወቅ አልተቻለም፡፡
ግን በፍንዳታውና ባስከተለው ተጓዳኝ ችግር በጠቅላላ ከ100 ሺህ ሰዎች በላይ ማለቃቸውን ብዙዎች ሰነዶች ይስማሙበታል፡፡
የእሳቱ ገሞራው ፍንዳታ ያስረገውና ያቃጠለው የአመዱ ብናኝ ለብዙ ቀናት የፀሐይ ብርሃን ጋርዶ ቆይቷል፡፡
ከአህጉሩ አልፎ በሌሎች አህጉራትም ፀሐይ ቀለም ቀይ አድርጓት ታይቷል፡፡
የአመዱ ብናኝ የአየር ብክለት በማስከተሉ በቀጣዩ አመት ያለው የአየር ሙቀት መጠን በእጅጉ በመቀነሱ የዝናብ መጠን ቀንሶ ድርቀቅ ተከተለ፡፡
ከ10 እስከ 20 ሚሊዮን ቶን የሚደርስ ሰልፈር ፣ ወደአየር ሰለበተነ ከፍተኛ የአየር ብክለት ደርሷል፡፡
በደሴቱና በአካባቢው ባሉት ሃገሮች ፣እፀዋት የሚባል ነገር ሰለጠፋ ፣ ረሃብና በሽታ ተከትሎ ከፍንዳታው የተረፈውን ሰው ፈጀው፡፡
የእሳተ ገሞራው ፍንዳታ በዚያን ለት አላበቃም፡፡
በእንቅጥቃጤው የተጎዳው መሬት፣ በየጊዜው እየሰመጠ የሚያወጣው ድምፅ የሚያስከትለው አመድ እስከሐሞሌ ድረስ ሲያስቸግራቸው ቆይቷል፡፡
እስካሁን ፣በአስከፊነቱ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት የታምቦራ ተራራ እሳት ገሞራ ፈንድቶ ፣ አካባቢውን ካወደመ፣ 210 ዓመታት ተቆጠሩ፡፡
እሸቴ አሰፋ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
コメント