top of page

ታሪክን የኋሊት - መጋቢት 26 2017 - የጥቁሮች መብት ተከራካሪ ማርቲን ሉተር ኪንግ የተገደለበት ቀን

  • sheger1021fm
  • Apr 4
  • 2 min read

ጀምስ ኧርል ሬይ ዝነኛውንና እውቁን የጥቁሮች መብት ተከራካሪ ማርቲን ሉተር ኪንግን የገደለው በ1960 ዓ.ም በዛሬ ቀን ነበር፡፡


ጀምስ ኧርል ሬይ፣ የ36 ዓመቱን ማርቲን ሉተር ኪንግን የገደለው ሜምፊስ በሚገኘው የሎሬን ሆቴል በረንዳ ላይ ቆሞ በነበረበት ጊዜ ነው፡፡


የ36 ዓመቱ ኧርል ሬይ፣ በተለያዩ ወንጀሎች እየተከሰሰ ሲታሰር የቆየ ነጭ አሜሪካዊ ነው፡፡


ማርቲሉ ሉተር ኪንግ የጥቁሮቹን መብት ለማስከበርና ተገላይነታቸውን ለማስቀረት አድማና አመፅ ያስከተለ ፣ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በመምራቱ፣ ሲታሰርና የግድያ ዛቻ በተደጋጋሚ ሲደርሰው ቆይቷል፡፡


የፌዴራሉ ምርመራ ቢሮ /ኤፍ ቢ አይ/ ሀላፊ የነበረው ሁቨርም ቢሮው ድረስ እየጠራ ማስጠንቀቂያ ሲሰጠው እንደነበር ታውቋል፡፡


በተገደለበት ቀን ዋዜማ፣ ወደ ሜምፌስ ለመሄድ የሚሳፈርበት አይሮፕላን የቦምብ ጥቃት ሊደርስበት ታስቧል በሚል ጥርጣሪ፣ ከብዙ ፍታሻና ጥንቃቄ በኋላ ነበር ዘግይቶ እንዲበር የተፈቀደለት፡፡

በሜምፊስ አድማ ለጀመሩት የፅዳት ሰራተኞች ካደረገው እስከ ዛሬም ድረስ ከሚደነቅለት ንግግሩ ማርቲን መጨረሻው እንደተቃረበ ተረድቶት ነበር፡፡


በንግግሩ ላይ በሽተኛ ከሚላቸው የነጭ አክራሪዎች የሞት አደጋ እንደታሰበለት ተናግሩዋል ፡፡

በዝግጅቱ መጨረሻም ድምፃዊ ቤን ብሪንች “የከበርከው አምላኬ እጄን ያዘኝ” የሚለውን ዘፈን እንዲዘፍን ጠይቆታል፡፡


ጀምስ ሬይ፣ ማርቲን ሉተር ካረፈበት ሆቴል ፣ ትይዩ፣ መንገዱን ተሻግሮ ካለው የሆቴል ክፍል ያዘ፡፡


በመታጠቢያ ቤቱ ገብቶ በመፀዳጃ ሳህኑ ላይ ቆሞ መስኮቱን ከፈተ፡፡


በትይዩም በሁለተኛ ፎቅ በረንዳ ላይ ፣ማርቴን ሉተር ንፋስ ለመቀበል ቆሞ ሲያየው ተኮሰ፡፡

የተኮሳት አንድ ጥይት፣ የሉተርን ጉንጭ መትታ ፣ በጆሮው አልፋ ትከሻውን መታችውና ወደቀ፡፡


ከተኩሱ በኋላ ሬይ ጠመንጃውንና እቃውን ጥሎ ከሆቴሉ ወጥቶ ሲሸሽ ታየ፡፡

የጣት አሻራውም በእቃዎቹ ላይ ተገኘ፡፡


ፖሊስ አልያዘውም፡፡


የሉተር ቤተሰቦች ሬይ መልዕክተኛ እንጂ የግድያው ተባባሪ ፖሊስ ነው ብለው አመለክተው ነበር፡፡


ሬይ ፣ ከሜምፊስ ሸሽቶ ፣አስራ አንድ ሰዓት ነድቶ፣ ቤቱ ወዳለበት አትላታ ደረሰ፡፡

እቃውን ይዞ ወደ ካናዳ ሄደ፡፡


በሐሰተኛ ስም የካናዳ ፓስፖርት ይዞ ወደ እንግሊዝና ፖርቹጋል ሄደ፡፡


እንደገና ወደ እንግሊዝ ሲመለስ፣ አይሮፕላን ጣቢያ ተያዘ፡፡


ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ ሌላ ፓስፖርትም ይዞ ተገኝቷል፡፡


ሬይ እጁ ተይዞ ለአሜሪካ ተላልፎ ተሰጠ፡፡


የሜምፌስ ፍርድ ቤት ፣ጥፋተኛ ነው ብሎ፣ 99 አመት ፈርደበት፡፡


በተወለደ በ70 አመቱ በታሰረ 34 ዓመቱ በተፈጥሮ ህመም በእስር ላይ እንዳለ አረፈ፡፡


ሬይ በድላኛለች ባላት የአሜሪካ ምድር፣ እንዳይቀበር ስለተናዘዘ አስከሬኑ ተቃጠለ፡፡


ሬይ ሉተርን ተኩሶ ከገደለ 57 ዓመት ሆነ፡፡


እሸቴ አሰፋ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page