ታሪክን በፎቶግራፍ የመሰነድ ባህል ዝቅተኛ መሆኑ ፣አብዛኞቹ የታሪክ ፎቶግራፎች በውጭ ዜጎች የተነሱ በመሆናቸው ታሪክን ከእነሱ እይታ አንጻር እንድንረዳ አድርጎናል ሲሉ ቱሪዝምና ታሪከን የሚሰንድ ተቋም የመሰረቱ ባለሞያ ነግረውናል፡፡
- Aug 5
- 1 min read
ሐምሌ 29 2018
ታሪክን በፎቶግራፍ የመሰነድ ባህል ዝቅተኛ መሆኑ ፣አብዛኞቹ የታሪክ ፎቶግራፎች በውጭ ዜጎች የተነሱ በመሆናቸው ታሪክን ከእነሱ እይታ አንጻር እንድንረዳ አድርጎናል ሲሉ ቱሪዝምና ታሪከን የሚሰንድ ተቋም የመሰረቱ ባለሞያ ነግረውናል፡፡

ፎቶግራፍ የታሪክ ክስተቶችን በፎቶ ከመሰነድ በተጨማሪ፣ የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን ለማስፋፋት አንደሚያግዝ አስርድተዋል፡፡
ፎቶግራፍ የሀገርን ታሪክ ሰንዶ ለቀጣይ ትውልድ በማሸጋገር ረገድ እንደ ከሥነ ፅሑፍና ሌሎችም የኪነ ጥበብ ዘርፎች ያልተናነሰ አቅም እንዳለው ይነገራል።
ፎቶግራፍ በአንድ ዘመን የነበረን የማህበረሰብ የአኗኗር ዘይቤ፣የከተማ ዕድገት፣የሀገር ገፅታና ታሪካዊ ማንነትን ይዞ የሚቀር፣ለትውልድም የሚያሸጋግር የጥበብ ዘርፍ ነው ይላሉ ባለሙያዎች።
ፎቶግራፍ ሀገር ትናንት የት እና እንዴት ነበረች የሚለውን ዝርዝር ታሪክ የሚናገር ቢሆንም በዚህ በዲጅታል ዘመን ላይ ሆነን እንኳን ታሪክን በፎቶ የመሰነድ ባህላችን ደካማ ነው ይላሉ።
አቶ ፍቅረሥላሴ ፀጋዬ የፎቶግራፍ ባለሙያ ሲሆኑ ቱሪዝምና ታሪክን በፎቶ የሚሰንድ ተቋም መስርተው እየሰሩ ነው።
የትናንትዋን ኢትዮጵያ የሚናገሩ ፎቶግራፎቻችን ሁሉ በምዕራባውያን ፎቶግራፈሮች የተነሱ ናቸው ይላሉ አቶ ፍቅረሥላሴ ።
"ጥንታዊቷን አዲስ አበባን እና ሰፈሮቿን የሚያሳዩ ፎቶግራፎች ያነሱት የውጪ ሰዎች ናቸው፣ የራስን ሀገር ታሪክ በውጪ ሀገር ሰው አይን ማየት የታሪክ መዛባት ያመጣል" ይላሉ።
"ያኔ እንኳን ኢትዮጵያውያን ቴክኖሎጂው ስለሌላቸው ይሆናል እንበል፣ዛሬ ለምንድነው የሀገራችንን ሁነት ፎቶግራፍ እያነሳን ታሪክ የማንሰንደው፣ዲጂታል ቱሪዝምንም የማናስፋፋው" ሲሉ ይጠይቃሉ።
"ዛሬ እንኳን በስልኮቻችንን የምናነሳቸው ፎቶግራፎች ውበት ላይ ያተኮሩ ናቸው፣ ታሪክ ደግሞ ውበት ብቻ አይደለም አማረም አላማረም ሁሉም የሀገር ገፅ በፎቶግራፍ ለታሪክ መሰነድ አለበት" ይላሉ።
የፎቶግራፍ ባለሙያው አቶ ፍቅረሥላሴ ፀጋዬ በየቦታው ሰዎች የሚያነሷቸውን ፎቶግራፎች እየሰበሰበ የሚሰንድ መንግስታዊ ተቋም ቢኖር የሚል ሃሳብም ያቀርባሉ።
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ....
ንጋት መኮንን
_edited.jpg)




Comments