top of page

ታህሳስ 9፣2017 - የውጭ ምንዛሪ እንደልብ በማይገኝበት ሁኔታ የፍራንኮ ቫሉታ መከልከሉ የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋቸውም እንዲንር አያደርግም ወይ?

መሰረታዊ ሸቀጦች የሚባሉት እነ ዘይት፣ ዱቄት፣ ሩዝ፣ መኮሮኒ፣ ፓስታ፣ ከገበያው እየጠፋ፣ ዋጋቸውም አልቀመስ እያለ ሲመጣ ፍራንኮ ቫሉታ መፈቀዱ ይታወቃል፡፡


ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ የተደረገው #የማክሮ_ኢኮኖሚ ማሻሻያም፣ ማሻሻያው ከስኬት እንዲበቃ ብሎ ከፈቀዳቸው መካከል ይሄው ፍራንኮ ቫሉታ ይገኙበታል፡፡


ፍቃዱ ግን ሁለት ወር በቅጡ ሳይሞላው፤ ነገር እያበላሸ ነው ተብሎ እንዲቀር ተደርጓል፡፡


#ፍራንኮ_ቫሉታ አላማውን ስቶ የሀገር ሀብት የማሸሺያ ስልት እየሆነ መምጣቱ፣ በፍራንኮ ቫሉታ ስም አስመጪም የጥቁር ገበያው ውስጥ መሳተፉ ተነገረ፡፡


በፍራንኮ ቫሉታ ይገቡ የነበሩ ሸቀጦችን ግን አስመጪዎች ከባንኮች የውጭ ምንዛሪ እየወሰዱ ማስመጣት እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡


አሁንም ቢሆን የውጭ ምንዛሪ እንደልብ በማይገኝበት ሁኔታ የፍራንኮ ቫሉታ መከልከሉ የመሰረታዊ ሸቀጦች እንዲጠፋ፣ ዋጋቸውም እንዲንር አያደርግም ወይ?


ዘላቂ መፍትሄውስ ምንድነው?


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…





ንጋቱ ሙሉ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Kommentarer


bottom of page