ታህሳስ 9፣2017 - ''ከምክክሩ በኋላ በኦሮሚያ ለብዙ ምስቅልቅል ምክንያት የሆነው ግጭት ይቆማል የሚል ተስፋ አለን'' የምክክር ተሳታፊዎች
- sheger1021fm
- Dec 18, 2024
- 1 min read
ከሀገራዊ ምክክሩ በኋላ በኦሮሚያ ክልል ለብዙ ምስቅልቅል ምክንያት የሆነው ግጭት ይቆማል የሚል ተስፋ አለን ሲሉ የምክክር ተሳታፊዎች ተናገሩ።
ተሳታፊዎቹ ይህን የተናገሩት ዛሬ በአዳማ ከተማ ሦስተኛ ቀኑን በያዘው የምክክር ምዕራፍ ላይ ነው።
በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ባለው የምክክር መድረክ ተሳታፊዎችን ከምክክሩ ምን እንደሚጠብቁ ጠይቀናቸዋል።
ተሳታፊዎቹ ‘’ከምክክሩ ቡኋላ በክልሉ የቀጠለው ግጭት መፍትሔ ያገኛል ብለን እንጠብቃለን’’ ብለዋል።
ትምህርት እንዲቋረጥ፣ የጤና ተቋማት አገልግሎት እንዳይሰጡ ሰዎች ከቦታ ቦታ እንዳይቀሳቀሱ እንቅፋት የሆነው በክክሉ ያለው ግጭት ከምክክሩ ብኋላ መፍትሔ ያገኛሉ ብለን እንጠብቃለን ብለውናል።

ምክክሩ ውጤታማ እንዲሆንም ከምክክር ሂደቱ እራሳቸውን ያገለሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና በትጥቅ ትግል ላይ ያሉ አካላት እንዲካተቱ ማድረግ ከሀገራዊ ምክክር ኮምሽን ይጠበቃል ብለዋል።
ሀገራዊ ምክክር ኮምሽን በበኩሉ በተደጋጋሚ ሁሉም አካላት በምክክሩ እንዲሳተፉ ተደጋጋሚ ጥሪዎችን እያደረኩ ነው ሲል መናገሩ ይታወሳል።
በአዳማ ከተማ ገልማ አባገዳ ውስጥ እየተካሄደ ባለው የምክክር ምዕራፍ ላይ ከ356 ወረዳዎች የተወከሉ ከ7,000 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተካፈሉ ይገኛሉ።
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comentarios