top of page

ታህሳስ 8፣2017 - የመከላከያ ሚ/ር የሰራዊት አባላት ምልመላ በሕግ በተቀመጡት መስፈርቶች መሠረት ብቻ የተከናወኑ ስለመሆናቸው በማረጋገጥ የሚረከብ መሆኑን አሳውቆኛል ሲል ኢሰመኮ ተናገረ

የመከላከያ ሚኒስቴር የሚከናወኑ የሰራዊት አባላት ምልመላ ሥራዎች በሕግ በተቀመጡት መስፈርቶች መሠረት ብቻ የተከናወኑ ስለመሆናቸው በማረጋገጥ የሚረከብ መሆኑን በደብዳቤ አሳውቆኛል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ተናገረ፡፡


ከመከላከያ ሰራዊት መስፈርቶች ውጪ፣ “ለምልመላ” በሚል #ሕፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎችን በግዳጅ በመያዝ የተሳተፉ፣ የተያዙ ሰዎችን ለመልቀቅ የገንዘብ ክፍያ የጠየቁ ወይም የተቀበሉ እንዲሁም ይህንን ድርጊት የመከላከልና የመቆጣጠር ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ የጸጥታና አስተዳደር አካላት ላይ ተገቢው ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ኢሰመኮ በለፈው ሳምንት ማሳሰቡ ይታወቃል።

በክልሎች የሚከናወኑ #የመከላከያ_ሰራዊት_አባላት ምልመላ ሥራዎች በሰራዊቱ መስፈርቶችና የአሠራር ሥርዓቶች መሠረት ብቻ ሕግን በተከተለ እና ሰብአዊ መብቶችን ባከበረ ሁኔታ መከናወናቸው እንዲረጋገጥ ምክረ ሐሳብ ሰጥቶ ነበረ፡፡


በምርመራው ግኝቶች እና ምክረ ሐሳቦች ላይ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሜቴ እና ከውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች እና አባላት ጋር ኅዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ምክክር ማካሄዱን ኢሰመኮ ተናግሯል።



''የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. #መከላከያ_ሚኒስቴርም በሁሉም ክልሎች የሚከናወኑ የሰራዊት አባላት ምልመላ ሥራዎች በሕግ በተቀመጡት መስፈርቶች መሠረት ብቻ የተከናወኑ ስለመሆናቸው በማረጋገጥ የሚረከብ መሆኑን ለኢሰመኮ ኅዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ደብዳቤ ደርሶኛል'' ብሏል ኢሰመኮ።


በተለይም በ2017 ዓ.ም. እየተደረገ ያለውን ምልመላ አፈጻጸም ለመፈተሽ ከከፍተኛ ሙያተኛ መኮንኖች የተውጣጣ ከ7 እስከ 12 አባላት ያሉት ኮሚቴ አዋቅሮ በማጣራት መስፈርቶቹን የሚያሟሉትን ብቻ ለይቶ ወደ ማሰልጠኛ ተቋማት ማስገባቱን እና ይህ ከመሆኑ አስቀድሞ በክልሎች በተከናወነው የምልመላ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች ካሉ ከክልሎች ጋር በመነጋገር ለማጣራት የሚቻል መሆኑን ሚኒስቴሩ መናገሩ ኢሰመኮ አስረድቷል።


ኢሰመኮ በክልሉ ተጠያቂነትን እንዲያረጋግጥ እና በቀጣይ ተመሳሳይ ጥሰቶች እንዳይፈጸሙ ለማድረግ የሚያስችሉ እርምጃዎችን እንዲወስድ የሚያደርገውን ጥረት እና ውትወታ እቀጥላለሁ ብሏል።



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


bottom of page