ከወራቶች በፊት ጅቡቲ ኢትዮጵያ የታጁራን ወደብ እንድታስተዳድረው መፍቀዷ ይታወሳል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንትም በአዲስ አበባ መግለጫ የሰጡት የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የአፍሪካ ህብርት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዕጩ ተወዳዳሪ መሀመድ አሊ የሱፍ፤ ሀገራቸው ኢትዮጵያ #የታጁራን_ወደብ እንድታስተዳድረው ባቀረበችው ውሳኔ አሁንም የአቋም ለውጥ እንዳላደረገች ማረጋገጣቸው ተዘግቧል፡፡
ለመሆኑ ኢትዮጵያ የታጁራን ወደብ ታስተዳድረው ማለት ምን ይሆን፤ ጥቅሙስ ምንድነው?
ሸገር ራዲዮ በጉዳዩ ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሎጀስቲክስ መምህር የሆኑት ማቲዮስ ኢንሰርሞን (ዶ/ር) አነጋግሯል፡፡
መምህሩ በመንግስት በኩል እስካሁን የተሰጠ ምላሽ ባይኖርም በጅቡቲ በኩል ለኢትዮጵያ የቀረበላት ግብዣ ጥቅም እንዳለው ይናገራሉ፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments