top of page

ታህሳስ 8፣2017 - መንግስት ከብሔራዊ ባንክ መውሰድ የሚችለው ብድር ላይ ገደብ የሚጥለው አዋጅ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ፀደቀ

መንግስት ከብሔራዊ ባንክ መውሰድ የሚችለው ብድር ላይ ገደብ የሚጥለው አዋጅ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ፀደቀ፡፡


ከገደቡም በላይ መንግስት የወሰደውን ብድር በአንድ ዓመት ውስጥ ካልከፈለ ለሌላ ጊዜ ብድር ሊከለከል ይችላል ተብሏል፡፡፡


በአዋጁ መሰረት ብሔራዊ ባንክ ከዚህ በኋላ ዋና እና ቀዳሚው ስራዬ ዋጋ ማረጋጋት ነው ብሏል፡፡


በተጨማሪም በህገወጥ መንገድ ስራ ላይ ይውላል ተብሎ የታመነበት ፈንድ ወይም ተቀማጭ ገንዘብ ካለ ብሔራዊ ባንክ ለ10 ቀን የማገድ ስልጣን አለው ተብሏል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ትዕግስት ዘሪሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


bottom of page