top of page
  • sheger1021fm

ታህሳስ 8፣ 2015- በሩሲያ እና ዩክሬይን መካከል የተከሰተውን ጦርነት የንግድ እንቅስቃሴን የምግብ አቅርቦትና የነዳጅ ዋጋ ላይ ተፅዕኖ በመፍጠር የአለም ምጣ


በሩሲያ እና ዩክሬይን መካከል የተከሰተውን ጦርነት የንግድ እንቅስቃሴን የምግብ አቅርቦትና የነዳጅ ዋጋ ላይ ተፅዕኖ በመፍጠር የአለም ምጣኔ ሀብትን ምስቅልቅሉ ውስጥ ከቶታል፡፡


በአገር ውስጥም ከሁለት ዓመት በላይ የዘለቀው ጦርነት ምጣኔ ሐብቱን ክፉኛ ፈትኖታል፡፡


ይህንን ያሉት የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ፍቅሩ ዴክሲሳ ናቸው፡፡


ከውስጥም ከውጭም ምጣኔ ሐብታዊ ፈተናው በበረታበት የ2014 የበጀት አመት በተለያዩ መመዘኛዎች ከፍተኛ ትርፍ አስመዝግቤያለሁ ሲል የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ተናግሯል፡፡


ባንኩ የ2014 የስራ ዘመን አጠቃላይ ሀብቴ 114.6 ቢሊየን ብርን ተሻግሯል ብሏል፡፡


ባንኩ 18ኛ የባለአክሲዮኖች አመታዊ እና 10ኛው ድንገተኛ ጉባኤውን ዛሬ በአዳማ አካሂዷል፡፡


በጠቅላላ ጉባኤው ላይ የባንኩን የስራ አፈፃፀም በተመለከተ ማብራሪያውን ያቀረቡት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢው ዶ/ር ፍቅሩ ዴክሲሳ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በሁሉም መለኪያዎች አመቱን በስኬት አጠናቀዋል ብለዋል፡፡


የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 114.6 ቢሊየን ብር አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘቡም 96.7 ቢሊየን ብር ደርሷል ብለዋል፡፡


የቦርዱ ሰብሳቢ ሲናገሩ እንደሰማነው አጠቃላይ የባንኩ ሀብት ካለፈው ዓመት በ41 በመቶ፣ ተቀማጩ ደግሞ በ36 በመቶ ጨምሯል፡፡


ያልተሳካና የተበላሸ ብድር መጠኑ ባለፈው አመት ከነበረበት 2.2 በመቶ ወደ 2.03 በመቶ ዝቅ ማለቱን ሰምተናል፡፡


በውጪ ምንዛሬ በኩልም ባንኩ በዓመቱ 438.2 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር አግኝቷል ተብሏል፡፡


ይህም ካለፈው ዓመት የ27 በመቶ ጭማሪ አለው፡፡


በተጠናቀቀው አመት የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ከሰራው ስራ በአጠቃላይ ከግብር በፊት 2.84 ቢሊየን ብር ትርፍ አግኝቻለሁ ብሏል፡፡


መጪውን ጊዜ ታሳቢ ያደረገ፣ የውጪ ባንኮች ወደ አገር ውስጥ ገብተው ስራ ቢጀምሩ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቀጠል በሚያስችለው ልክ እየተዘጋጀ ስለመሆኑ በጉባኤው ላይ ሲነሳ ሰምተናል፡፡


ቴዎድሮስ ወርቁ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

Recent Posts

See All

በኢትዮጵያ የካፒታል ወይም ድርሻዎች ገበያ መሳተፍ ለሚፈልጉ ተቋማት ከ3 እስከ 6 ወር ባለው ጊዜ ፍቃድ መስጠት ይጀመራል ተባለ። ፍቃድ የሚሰጣቸውን ተቋማት ለመለየት መመሪያ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ታዬ ተናግረዋል። የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ የተመለከተ ምክክር

በጋሞ ዞን ውስጥ የሚገኙ የዘይሴ እና የቁጫ ብሔረሰቦች ከፍተኛ በደል እየደረሰባቸው ነው ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑ እንደራሴዎች ተናገሩ፡፡ ለሚደርሰው በደል ዋነኛው ምክንያት የአካባቢው ነዋሪዎች በምርጫ ወቅት የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲን በመምረጣቸው ነው ብለዋል፡፡ ንጋቱ ሙሉ ሸገርን ወሬዎች፣ መ

በአፋርና በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት የወደሙ ት/ቤት መልሶ መገንቢያ እስካሁን 2.8 ቢሊየን ብር ተሰብስቧል ተባለ፡፡ በጦርነቱ ከ300 ት/ቤቶች በላይ ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ይታወሳል፡፡ ተመስገን አባተ ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

bottom of page