top of page

ታህሳስ 7፣2017 - የኦሮሚያ ክልል የምክክር ተሳታፊዎች የኦሮሞ ህዝብ ለ150 ዓመታት ሲጠይቅ የነበረው ጥያቄ መልስ እንዲያገኝለት አጀንዳ ሆኖ እንዲቀርብ አባገዳዎች ጠየቁ

የኦሮሚያ ክልል የምክክር ተሳታፊዎች የኦሮሞ ህዝብ ለ150 ዓመታት ሲጠይቅ የነበረው ጥያቄ መልስ እንዲያገኝለት አጀንዳ ሆኖ እንዲቀርብ አባገዳዎች ጠየቁ፡፡


አባ ገዳዎች ይህን የጠየቁት ዛሬ በአዳማ ከተማ የሀገራዊ ምክክር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ምርቃት ላይ ነው፡፡፡


አባ ገዳዎቹ የኦሮሚያ ህዝብ ለ150 ዓመታት ሲጠይቃቸው የነበሩ ጥያቄዎች አንድም እንዳይዘነጉ ለምክክሩ ተሳታፊዎችን አሳስበዋል፡፡


‘’በምክክሩ የኦሮሞ ሕዝብ የዘመናት ጥያቄ ናቸው የተባሉት የቋንቋ፣ የወሰን ጥያቄዎች ይፈታሉ ብለን እናምናለን’’ ብለዋል፡፡

‘’የአዲስ አበባ ጉዳይ የኦሮሞ ህዝብ የዘመናት ጥያቄ ነው’’ ያሉት አባገዳዎቹ ይህም በምክክሩ እንዲፈታ ጠይቀዋል፡፡


የምክክሩ ተሳታፊዎች የወከሉት የኦሮሞ ህዝብ ተቆራርጠው የቀሩት የመሬት ጥያቄዎች፣ የወሰን ጥያቄዎች እንዲፈቱ አጀንዳ ሆነው እንዲያቀርቡ አሳስበዋል፡፡


ኦሮሚኛ ቋንቋም የፌዴራል የስራ ቋንቋ እንዲሆን አባ ገዳዎቹ ለተሳታፊዎቹ ‘’አጀንዳ’’ አድርጋችሁ አቅርቡ ብለዋቸዋል፡፡

አባ ገዳዎቹ የኦሮሞ ህዝብ መልስ እንዲያገኝ ጠይቁ ባሉበት ወቅት፤ በምክክር ሂደት ላይ ለመሳተፍ በስታዲየም የተገኙት ሰዎች በጭብጨባና በፉጨት ድጋፋቸውን አሳይተዋቸዋል፡፡


በዛሬ በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ከተማ በተጀመረው የምክክር ምዕራፍ ከ356 ከክልሉ ወረዳዎች የተወከሉ ከ7,000 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወክለዋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Commentaires


bottom of page