ኢትዮጵያና ሶማሊያን ያስማሙት የቱርኩ ፕሬዘዳንት ራሲፕ ታይፕ ኤርዶሃን ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው፡፡
ኤርዶሃን ከሁለት ሳምንታት በኋላ በሚብተው የፈረንጆቹ 2025 የመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት ኢትዮጵያን እና ሶማሊያን እንደሚጎበኙ መናገራቸውን የቱርኩ አናዶሉ ፅፏል፡፡
ፕሬዘዳንት ኤርዶሃን የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድንና የሶማሊያው ፕሬዘዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድን አሸማግለው ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል፡፡
የኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የሶማሊያን ሉአላዊነት ባከበረ መልኩ እንዲሆን በሁለቱ ሀገራት በመሪዎች ደረጃ ባለፈው ሳምንት ስምምነት ተደርጓል፡፡
የአንካራው ስምምነት የተደረሰውም ሰባት ሰዓታት ከፈጀ ስብስብ በኋላ መሆኑን ኤርዶሃን ተናግረዋል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments