ታህሳስ 7፣2017 - በሰሜን ሸዋ ዞን ትምህርታቸውን ይከታተላሉ ተብለው ከታሰቡት ተማሪዎች፤ ትምህርታቸው እየተከታተሉ ያሉት ግማሽ ያህሉ እንደሆኑ ተነገረ
- sheger1021fm
- Dec 16, 2024
- 1 min read
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ትምህርታቸውን ይከታተላሉ ተብለው ከታሰቡት 318,000 ተማሪዎች ትምህርታቸው እየተከታተሉ ያሉት ግማሽ ያህሉ ናቸው ሲሉ ዞኑ ተናገረ፡፡
በክልሉ አሁን ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት በተለይ የሁለተኛ ደረጃ #ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እየሄዱ አይደለም ሲሉ የሰሜን ሸዋ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ፀጋዬ እንግዳ ወርቅ ነግረውናል፡፡
‘’የትምህርት ተቋማት #ከፖለቲካ_ነፃ መሆን አለባቸው’’ የሚሉት ሀላፊው ህፃናቱ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ሁሉም አካላት ሊያግዙን ያገባል ብለዋል፡፡
መምህራን ወደ ትምህርት ቤት የሚመጡ ተማሪዎች ባለመኖራቸው እና ባለማስተማራቸው ለስነ ልቦና ጫና ተዳርገዋል መባሉን ሰምተናል፡፡
በዞኑ የመፅሐፍ እና የትምህርት ቁሳቁስ ችግር እንደሌለ አቶ ፀጋዬ እንግዳ ወርቅ ተናግረዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ..
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments