top of page

ታህሳስ 7፣2017 - ም/ጠቅላይ ሚ/ር እና የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የነበሩት አቶ ደመቀ መኮንን "የአዳም ፋውንዴሽን" የተባለ ድርጅት አቋቋሙ

  • sheger1021fm
  • Dec 16, 2024
  • 1 min read

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ደመቀ መኮንን "የአዳም ፋውንዴሽን" የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት አቋቋሙ።


የፉውንዴሽኑ ይፋ የምስረታ ስነስርዓት በዛሬው ዕለት በሸራተን አዲስ ተካሄዷል።


አቶ ደመቀ መኮንን የመሰረቱተና በቦርድ ሊቀመንበርነት የሚመሩት "የአዳም ፋውንዴሽን"በአፍሪካ መቀንጨርን ለመዋጋት" እንደሚሠራ በስነስርዓቱ ላይ ተነግሯል።


በዝግጅቱ ላይ ንገግር ያደረጉት አቶ ደመቀ መኮንን በረዥሙ የስልጣን ቆይታቸው ከተገነዘቧቸውና ሲሰሩባቸው ከቆዩ ስራዎች መካከል አንደኛው "መቀንጨር" መሆኑን ጠቅሰዋል።


በዚህም መቀንጨርን ለመከላከል የተቋቋመውን ኮሚቴ ሲመሩ እንደነበር፣ የሰቆጣው የቃል ኪዳን ስምምነት ግቡን እንዲመታ በአመራር ቆይታቸው መስራታቸውን አስታውሰዋል።


የመንግስት ስልጣናቸውን ከለቀቁ ብኋላም የሁሉም ጉዳይ የሆነውን የመቀንጨርን መከላከል ላይ ለመስራት መወሰናቸውን አስረድተዋል።


በኢትዮጵያ ያለውን የምግብና የስርዓት ምግብ ፖሊሲ፣ የሰቆጣ ቃል ኪዳን ስመምነት የመሳሰሉት አና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የሌማት ትሩፋት በማጎልበት ከሀገሪቱ አልፎ በመላ አፍሪካ መቀንጨርን ለመከላከል ፋውንዴሽኑ እንደሚሰራ አቶ ደመቀ ተናግረዋል።

ቢግ ዊን፣ የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ)፣ ቢል ኤንድ ጌትስ ፋውንዴሽን፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን የፋውዴሽኑ አጋሮች መሆናቸውን በስነ ስርዓቱ ላይ ሲነገር ሰምተናል።


የአዳም ፋውንዴሽን ይፋዊ የምስረታ ስነ-ስርዓት ላይ ሚኒስትሮች፣ የአለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮች እና ሌሎችም ተገኝተዋል።


በኢትዮጵያ እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ከሆኑ አንድ መቶ ልጆች ስላሳ ዘጠኙ የቀነጨሩ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።


መቀንጨርን ለመከላከል ከእርግዝና አስከ ሁለት ዓመት ያለው ጊዜ የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት ወሳኝ መሆኑን ባለሞያዎች ይናገራሉ።


የአዳም ፈውንዴሽንን የመሰረቱት እና በቦርድ ሊቀመንበርነት የሚመሩት አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነትን ጨምሮ በተለያዩ ሀላፊት ላይ ለ30 ዓመታት ያህል ቆይተው ባለፈው ዓመት በገዛ ፍቃዳቸው መሰናበታቸው ይታወሳል።


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page