በቻድ በረሃ ውስጥ የ27 ስደተኞች አፅም ተገኘ፡፡
የስደተኞቹ አፅም የተገኘው በአንድ ፒክ አፕ መኪና ላይ እንደሆነ አለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ባለስልጣናት መናገራቸውን አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡
አፅማቸው የተገኘው ስደኞች የሞቱት ከዓመት ከ5 ወራት በፊት በጉዞ ላይ በነበሩበት ወቅት እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
ይጓዙባት የነበረች ፒክ አፕ መኪና መበላሸቷ በረሃ ላይ እንዳስቀራቸው ተገምቷል፡፡
በዚህ በረሃማ ስፍራ ረሃብ እና የውሃ ጥም ለሕልፈታቸው ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ተጠርጥሯል፡፡
IOM በነዚህ ስደተኞች መጥፎ ዕጣ ፈንታ በእጅጉ አዝኛለሁ ማለቱ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡
የኔነህ ከበደ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comentarios