top of page

ታህሳስ 4፣ 2015- በኢትዮጵያ በስራ ላይ ያሉ 37 የብረት አምራች ኩባንያዎች በ4 ወር ውስጥ ያመረቱት የብረት መጠን 142,65 ግድም ቶን ብቻ ነው ተባለ፡


በኢትዮጵያ በስራ ላይ ያሉ 37 የብረት አምራች ኩባንያዎች በ4 ወር ውስጥ ያመረቱት የብረት መጠን 142,65 ግድም ቶን ብቻ ነው ተባለ፡፡


የብረት አምራች ኩባንያዎቹ እናመርታለን ብለው ያቀዱት መጠን 1,118 ግድም ቶን መሆኑን ሰምተናል፡፡


በሐገር ቤት ፋብሪካ አቋቁመው ብረት እናመርታለን ብለው ወደ ስራ የገቡት አምራቾች በ4 ወር ውስጥ ያመረቱት የእቅዳቸውን 12 በመቶ መሆኑን ማዕድን ሚኒስቴር ለሸገር ነግረዋል፡፡


የብረታ ብረት አምራች ኢንዱስትሪዎች የ4 ወራት የስራ አፈፃፀማቸው ከሐምሌ እስከ ጥቅምት ወር ድረስ ነው፡፡


ከ37ቱ ብረት አምራች ኢንዱስትሪዎች ሐበሻ ብረት ፋብሪካ የእቅዱ 58.7 በመቶ በመሳካት ቀዳሚ ሆኗል፡፡


ሐበሻ የብረት አምራች ፋብሪካ በ4 ወር ውስጥ 19,961 ቶን ብረት ማምረቱን ከሪፖርቱ ተመልክተናል፡፡


በሁለተኛ ደረጃ ሴንቲኔል ብረት አምራች 19,139 ቶን አምርቷል፤ ይህም የእቅዱን 47.85 በመቶ ነው ተብሏል፡፡


በ3ተኛ ደረጃ በ4 ወር ውስጥ ስቲሊ RMI 13,208 ቶን ብረት አምርቷል፡፡

በዚሁ የጊዜ ማዕቀፍ አቅደው ምንም ሳያመርቱ ሪፖርታቸው በዜሮ የተመዘገቡ የብረት ፋብሪካዎች መኖራቸውንም ሰምተናል፡፡


ከ37 ብረት ፋብሪካዎች 5ቱ ምንም ሳያመርቱ በዜሮ ተመዝግበዋል፡፡


በዜሮ የተመዘገቡት ፋብሪካዎች ኤኮስ ስቲል፣ ድሬ ብረት ስታር ቢዝነስ ግሩፕ፣ ሴኖ ስቲል እና አያም የተባሉ ፋብሪካዎች ናቸው፡፡


በ4 ወር ውስጥ ሳቤ፣ ማሜ እና ፀሐይ ብረት አምራች ኢንዱስትሪዎች ዝቅተኛ ምርት እንዳቀረቡ ከሪፖርቱ ተመልክተናል፡፡


ተህቦ ንጉሴ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Comments


bottom of page