ታህሳስ 4፣ 2015
በናይጀሪያ ኢሞ ግዛት በምርጫ ፅህፈት ቤት ላይ ጥቃት ከሰነዘሩ ታጣቂዎች ሶስቱ በፖሊስ መገደላቸው ተሰማ፡፡
በፖሊስ የአፀፋ ተኩስ ከተገደሉት ሌላ ሁለቱ በስፍራው እንደተያዙ አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡
በታጣቂዎቹ ጥቃት የግዛታዊ የምርጫ ፅህፈት ቤቱ ሕንፃ ጉዳት ደርሶበታል ተብሏል፡፡
በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ላይ ስለደረሰው ጉዳት የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡
በኢሞ ግዛት በምርጫ ፅህፈት ቤቶች ላይ ጥቃት ሲሰነዘርባቸው በ2 ሳምንታት ጊዜ ይሄ 3ኛው ነው ተብሏል፡፡
ናይጀሪያ በመጪው የካቲት ወር ፕሬዝዳንታዊ፣ የግዛት እና የፓርላማ ምርጫ ለማካሄድ እየተዘጋጀች ነው፡፡
የኔነህ ከበደ

ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz
Comments