top of page

ታህሳስ 4፣ 2015የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ ዛሬ የፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳን የስልጣን ቆይታ በሚወስን ጉዳይ ተሰብስቦ ይመክራል ተባለ


የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ ዛሬ የፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳን የስልጣን ቆይታ በሚወስን ጉዳይ ተሰብስቦ ይመክራል ተባለ፡፡


ፕሬዝዳንቱ በፋላ ፋላ እርስታቸው ከሚገኝ በውጭ ምንዛሪ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ መዘረፉን ለመሸፋፈን ሞክረዋን መባሉ ጣጣ እንዳስከተለባቸው የአሜሪካ ድምፅ የእንግሊዘኛው አገልግሎት አስታውሷል፡፡


በዚህም ራሳቸው ከሚመሩት የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ANC) የፖለቲካ ማህበር አንዳንድ ወገኖች ሳይቀር ስልጣን እንዲለቁ ግፊት ሲደረግባቸው ሰንብቷል፡፡


የ ANC ከፍተኛ ሥራ አስፈፃሚ አካል ድጋፉ ለራማፎሣ እንደሆነ እወቁልኝ ብሏል፡፡


በፓርላማው ተከስሰው ስልጣን እንዲለቁ የውሳኔ ሀሳብ ቢቀርብ እንኳ በፓርላማው ተቀባይነት የማግኘቱ እድል የተጣበበ ነው ተብሏል፡፡


በደቡብ አፍሪካ ፓርላማ አብላጫዎቹን መቀመጫዎች የሚቆጣጠረው ANC መሆኑን ዘገባው አስታውሷል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Kommentare


bottom of page