top of page

ታህሳስ 30፣2017 - ቤንዚን በሊትር 10 ብር ጨመረ

  • sheger1021fm
  • Jan 8
  • 1 min read

ቤንዚን በሊትር 10 ብር ጨመረ።


በተጨማሪም በተለያዩ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ተነግሯል።


ይህንን የተናገረው የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነው፡፡


በተደረገው መሻሻያ መሰረትም ቤንዚን በሊትር 10 ብር ጭማሪ አሳይቷል፡፡


በዚህም 91 ብር 14 ሳንቲም የነበረው ቤንዚን 101 ብር ከ47 ሳንቲም ሆኗል፡፡

90 ብር ከ28 ሳንቲም የነበረው  ነጭ ናፍጣ  98 ብር ከ 28 ሳንቲም ሆኗል፡፡


90 ብር ከ 28 ሳንቲም የነበረው ኪሮሲን 98 ብር ከ98 ሳንቲም ሆኗል፡፡


100 ብር ከ 2 ሳንቲም የነበረው ቀላል ጥቁር ናፍጣ 5 ብር ጨምሮ 105 ብር ከ97 ሳንቲም ሆኗል፡፡


የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር ከነበረው 77 ብር ከ76 ሳንቲም የነበረው 109 ብር ከ56   ሆኗል፡፡


የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር "በወሩ መጨረሻ የነዳጅ ዋጋ ክለሳ ይሠራል” በሚል ተስፋ ነዳጅ ይዘው የተደበቁት ቦቴዎች አግኝቻለሁ ማለቱ ይታወሳል።


ጭማሪው ከዛሬ ታህሳስ 29፣2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን


ማንያዘዋል ጌታሁን

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page