ፈተና ከተቀመጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች ግማሾቹ ወደቁ።
ፈተናውን የተፈተኑት 10,257 ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ 5,095 ዎቹ የማለፊያ ውጤት አስመዝግበዋል፣ ቀሪዎቹ 50 በመቶ ደግሞ የተቀመጠውን የማለፊያ ነጥብ ማስመዝገብ አለመቻላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጣሰው ገብሬ ተናግረዋል።
ታህሳስ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ለከተማ አስተዳደሩ አመራር፣ ባለሞያዎች እና ሰራተኞች የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና መውሰዳቸው ይታወሳል።
መመዘኛ ፈተናውን የወሰዱ ዳይሬክተር እና ቡድን መሪዎች ቁጥር 4,213 ሲሆን የፈተናውን ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡት 34 በመቶ ወይም 1,422 የሚሆኑት ናቸው ተብሏል።
ለፈተና ከተቀመጠው አጠቃላይ ቁጥር 681 የሚሆነው በተለያየ የስነ ምግባር ጥሰት ከፈተና ውጪ መሆናቸውን እና 441 የሚሆኑት ደግሞ በፈተና ስፍራ አልተገኙም መባሉን ሰምተናል።
በተጨማሪም በፈተናው ውጤት ላስመዘገቡ የክዋኔ ክህሎት ስልጠና ላላለፉት ደግሞ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደሚሰጥ እቅድ መያዙን ሀላፊው አስረድተዋል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments