top of page

ታህሳስ  30፣2016  -  የባህር ማዶ ወሬዎች

 

የአለም የጤና ድርጅት ወደ ሰሜናዊ ጋዛ መድሐኒት ማቅረብ አልቻልኩም አለ፡፡

 

ድርጅቱ ወደ ስፍራው መድሐኒት ለማድረስ ከእስራኤል በኩል የደህንነት ዋስትና አላገኘሁም ማለቱን TRT ዎርልድ ፅፏል፡፡

 

የአለም የጤና ድርጅት ለሰሜናዊ የጋዛ ክፍል መድሐኒት ለማቅረብ የደህንነት ዋስትና እንዲሰጠው በተደጋጋሚ ጥያቄ ማቅረቡ ተጠቅሷል፡፡

 

ከእስራኤል በኩል ቀና ምላሽ ማግኘት አልቻልኩም ብሏል፡፡

 

በእስራኤል የጋዛ ዘመቻ ብዙዎቹ ሆስፒታሎች እና የጤና ተቋማት መውደማቸው ይነገራል፡፡

 

በስራ ላይ ያሉትም ቢሆን በመድሐኒት እና በሕክምና መሳሪያዎች አለመኖር ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዳልቻሉ ዘገባው አስታውሷል፡፡

 

 

የፍልስጤማውያኑ የጦር ድርጅት /ሐማስ/ በጋዛ የእስራኤል ጦር ታጋቾችን ለማስለቀቅ ያደረገውን ሙከራ አጨናገፍኩበት አለ፡፡

 

ሐማስ በመግለጫው የእስራኤል ጦር ታጋቾቹ ይገኙበታል ብሎ ወደ ጠረጠረው ቡሬጅ የስደተኞች መጠለያ ሰፈር ሀይሉን አሰማርቶ ነበር ማለቱን አናዶሉ ፅፏል፡፡

 

ከዚህ ሀይል ጋር ተተጋትገን በብዙዎቹ የእስራኤል ወታደሮቹ ላይ ጉዳት አድርሼቼዋለሁ ማለቱ በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

 

ሐማስ ከ3 ወራት በፊት ወደ እስራኤል በመዝለቅ ድንገት ደራሽ ጥቃት ባደረሰበት ወቅት ከ200 የማያንሱ ታጋቾችን ወደ ጋዛ ይዞ መምጣቱ ይነገራል፡፡

 

የተወሰኑትንም እስራኤል በፈታቻቸው ፍልስጤማውያን እስረኞች ልዋጭ ለቅቋቸዋል፡፡

 

አሁንም ከ136 የማያንሱ ታጋቾች በእጁ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

 

ሐማስ የእስራኤልን ጦር ታጋቾችን የማስለቀቅ ሙከራ አክሽፌያለሁ ስለማለቱ ከእስራኤል በኩል የተሰጠ አስተያየት የለም፡፡

 

 

የዩጋንዳ ሹሞች ከአገራቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚሰጥ ዲግሪ በናይጀሪያ ተቀባይነት ሊያጣ ነው መባሉን አስተባበሉ፡፡

 

የዩጋንዳ የከፍተኛ ትምህርት ብሔራዊ ምክር ቤት የበላይ ፕሮፌሰር ሜሪ አክዋኮል ይሄን ጉዳይ በሚመለከት ናይጀሪያ ያሳወቀችን ነገር የለም ማለታቸውን አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡

 

የቀረበላቸው ቅሬታ እንደሌለም ተናግረዋል፡፡

 

ሰሞኑን ናይጀሪያ ከዩጋንዳ እና ከኬኒያ የሚመጡ ዲግሪዎችን ላለመቀበል ልትወስን ነው ተብሎ ነበር፡፡

 

በዩጋንዳ በአፍሪካ ታዋቂነቱ ከፍ ያለው የማካሬሬ ዩኒቨርስቲ ከዚህ ቀደም ያልተገቡ እና ሐሰተኛ ዲግሪዎች ተሰጥተው እንደሆነ በመመርመር ላይ እንደሆነ በዘገባው እግረ መንገድ ተጠቅሷል፡፡

 

ካያምቦንጎ ዩኒቨርስቲ ግን እሱ ያልሰጣቸው እና በስሙ ተመሳስለው የተሰሩ ድግሪዎች መገኘታቸውን የስራ መሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

 

የኔነህ ከበደ

 

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 



 

 

Comentarios


bottom of page