top of page

ታህሳስ 3/2018 ባለፉት 4 ወራት በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ የኮንትሮባንድ እቃዎች ቁጥር መጨመሩን የገቢዎች ሚኒስቴር ተናገረ፡፡

  • sheger1021fm
  • Dec 12, 2025
  • 1 min read


የገቢዎች ሚኒስቴር ይሄን ያለው ዛሬ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ለፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ4 ወር የስራ ክንው ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡


ሪፖርቱን ያቀረቡት የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ከገቢ ኮንትሮባንድ ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ ፣ ከወጪ ኮንትሮባንድ ደግሞ 0.6 ቢሊየን ብር ማዳን መቻሉን ተናግረዋል፡፡


በድምሩ 8.7 ቢሊየን ብር የሚያወጣ የኮንሮባንድ እቃ መያዙን ተናግረዋል፡፡


የገቢ ኮንትሮባንድ በእጥፍ መጨመሩን የተናገሩት ሚኒስትሯ መድሃኒት፣ አልባሳት ጨርቃ ጨርቅ ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና የማዕድን ውጤቶች ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ አስረድተዋል፡፡


ባለፉት 4 ወራት 27 ኪሎ ግራም የሚመዝን ጥፍጥፍ ወርቅ መያዙንም ሚኒስትሯ አክለዋል፡፡


የወጪ ኮንትሮባንድ አብዛኛውን ድርሻ የሚይዘው የግብርና ምርት ነው የተባለ ሲሆን ባለፉት 4 ወራት ቅናሽ ማሳየቱ ተጠቁሟል፡፡


ሚኒስትር ዓይናለም በኮንትሮባንድ ሂደት ሲሳተፉ የተያዙ 353 ሰዎች በቁጥጥር  ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ እንደሚገኝ ለቋሚ ኮሚቴው አስረድተዋል፡፡


በሌላ በኩል ባለፉት 4 ወራት ሚኒስቴር መ/ቤቱ 482.5 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡ ተናግሯል፡፡

ይህም የእቅዱ 106 በመቶ ነው ተብሏል፡፡


ባለፉት 4 ወራት 444.3 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እንደነበር ያስታወሱት ሚኒስትሯ 482.5 ቢሊየን ብር ገቢ ሰብስበናል ብለዋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

  

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page