ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግፕት የሶማሊያን ሉዓላዊነት ባከበረ መልኩ እንዲሆን ተስማማች፡፡
የኢትዮጵያና የሶማሊያ መሪዎች ባደረጉት ሰምምነት መሰረት ሶማሊያ በዓለም አቀፍ ህጎች፣በመንግስታቱ ድርጅት ቻርተር አና በአፍሪካ ህብረት ህግ ላይ በሰፈረው የሶማሊያን ሉዓላዊነትን ባከበር መልኩ በኮንትራት፣በሊዝ ወይንም በሌሎች ሞዳሊቲዎች ኢትዮጵያ የባሕር በር ለመግኘት የሚያስችላት ስምምነት ተደርጓል፡፡
ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ አደራድረው ድርድሩ በስምምነት መጠናቀቁ ተሰምቷል።
የቱርክ ኮሙኒኬሽን መስሪያቤት ስምምነቱን በመለከተ በኤክስ (x) ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ ስመምነቱ "የአንካራ ስምምነት" እንደተባለ አስረድቷል"።
በስመምነቱ መሰረት የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በአለም አቀፍ ህጎች፣በመንግስታቱ ድርጅት ቻርተር አና በአፍሪካ ህብረት ህግ ላይ በሰፈረው መሰረት አንዳቸው የአንዳቸውን ሉዓላዊነት፣ አንድነት፣ ነፃነት እና የግዛት አንድነት ለማክበር ቁርጠኛ ነን ብለዋል።
በወዳጅነት እና በመከባበር መንፈስ ልዩነቶችን እና አከራካሪ ጉዳዮችን በመተው፤በመተጋገዝ ለጋራ ብልጽግና ለመስራት መስማማታቸው ተጠቅሷል።
ከዚህ በተጨማሪም ሶማሊያ በአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደሮች ለከፈሉት መስዋዕትነት እውቅና እሰጣለሁ ብላለች።
ስምምነቱ ኢትዮጵያ አስተማማኝ የባሕር መተላላፊያ ማግኘቷ የሚኖረውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታን ሁለቱ አገራት ዕውቅና ይሰጣሉ ይላል።
የኢትዮጵያ አስተማማኝ እና ቀጣይነት ያለው የባህር በር እንድታገኝ የሚያስችሉና ሁለቱንም ሀገራት ተጠቃሚ የሚያደርጉ የንግድ ሁኔታዎችን፣ የኮንትራት፣ ውል፣ የሊዝ እና መሰል ዘዴዎችን በጋራ ለማዘጋጀት ተስማምተዋል።
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና እና ዘላቂነት ያለውየባህር በር መዳረሻ እንዲኖራት የተስማሙ ሲሆን ይህም የሚሆነው በሉዓላዊ የሶማሊያ መንግሥት ስልጣን ስር ነው ተብሏል።
ይንንም ከግብ ለማድረስ በቱርክ አመቻችነት የካቲት ወር ከማለቁ በፊት ቴክኒካል ድርድር እንዲጀመር እና በ4 ወራት ውስጥ እንዲጠናቀቅ ተስማምተዋል።
ሁለቱ ወገኞች በስምምነቶቹ አተረጓጎም እና በአተገባበር ላይ ያሉ ልዩነቶችን በቱርክ አገዥነት በውይይት እና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ተስማተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር ባለፈው ዓመት ጥር ላይ ባደረገችው የባህር በር የማግኘት ስመምነት የተነሳ ሶማሊያ ልዑላዊነቴ ተደፍሯል ብላ ዲፕሎማሲያዊ ግኑኝነቱ ደፍርሶ ቆይቷል።
ሁለቱ ሀገሮች በቱርክ አሸማጋይነት በሚኒስትሮች ደረጃ አንካራ ላይ ያልተሳከ ሁለት ዙር ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።
ትናንትና የተደረገው ድርድር በመሪዎች ደረጃ የተደረገ ሲሆን በስምምነት መጠናቀቁም ተሰምቷል።
Comments