top of page
  • sheger1021fm

ታህሳስ 3፣ 2015- አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ በ2014 በጀት ዓመት የተጣራ 344.9 ሚሊዮን ብር ማትረፉን ተናገረ

Updated: Dec 13, 2022


ታህሳስ 3፣ 2015


አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ በ2014 በጀት ዓመት የተጣራ 344.9 ሚሊዮን ብር ማትረፉን ተናገረ፡፡


ትርፉ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ27.1 በመቶ ዕድገት አሳይቷል ተብሏል።


ባንኩ ይህን ትርፍ ያገኘሁት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ባጋጠመው ጦርነት እና የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ የኮረና ወረርሽኝ፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ንረት እና ሌሎች ተፅዕኖዎችን ተቋቁሜ ነው ብሏል፡፡


ባንኩ በበጀት ዓመቱ 1.5 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን የተናገረ ሲሆን፤ ይህም ባለፈው ዓመት ከተገኘው ጋር ሲነፃፀር የ32 በመቶ ወይንም የ365 ሚሊዮን ብር ዕድገት አሳይቷል ሲል በሪፖርቱ ተናግሯል።


አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ ለደምበኞቹ የሰጠው አጠቃላይ ብድር 6.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል ብሏል።


ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የብር 1.6 ቢሊዮን ብር ወይም የ35 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ጠቅሷል፡፡

ከፍተኛው ብድር የተሰጠው ለውጭ ንግድ ሲሆን 47 በመቶ ድርሻ ይይዛል ብሏል፡፡


የሀገር ውስጥ ንግድና አገልግሎት 19 በመቶ፣ ኮንስትራክሽን 15 በመቶ፣ ማምረቻ 8 በመቶ፣ የገቢ ንግድ 6 በመቶ በመያዝ ሌሎች ተበዳሪ ዘርፎች መሆናቸውን ከሪፖርቱ ተመልክተናል፡፡


ባንኩ በሂሳብ ዓመቱ መጨረሻ በደምበኞች እጅ ከሚገኘው ብድር ውስጥ 96.8 በመቶ ጤናማ ብድር ነው ያለ ሲሆን የተበላሸ ብድር 3.2 በመቶ ነው ይህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ካስቀመጠው 5 በመቶ መስፈርት በታች መሆኑን አስረድቷል።


ጠቅላላ ሀብቴ 10.8 ቢሊዮን ብር፣ አጠቃላይ ካፒታሌ ድግሞ 2.2 ቢሊዮን ብር ደርሶልኛል ብሏል፡፡


ብንኩ ማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው 3 ሚሊዮን ብር፤ ለተስፋ አዲስ የህጻናት ካንሰር ህሙማን መረጃ ማእከል 60 ሺ ብር ድጋፍ ማድረጉን ተናግሯል፡፡


እንዲሁም የውጭ ሀገራት ገንዘቦችን ደንበኞች በባንኩ በኩል ሲቀበሉ እና ሲመነዝሩ ከተገኘው ገቢ 1.5 ሚሊዮን ብር ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰጥቻለሁ ብሏል፡፡


ንጋቱ ሙሉ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqzRecent Posts

See All

በኢትዮጵያ የካፒታል ወይም ድርሻዎች ገበያ መሳተፍ ለሚፈልጉ ተቋማት ከ3 እስከ 6 ወር ባለው ጊዜ ፍቃድ መስጠት ይጀመራል ተባለ። ፍቃድ የሚሰጣቸውን ተቋማት ለመለየት መመሪያ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ታዬ ተናግረዋል። የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ የተመለከተ ምክክር

በጋሞ ዞን ውስጥ የሚገኙ የዘይሴ እና የቁጫ ብሔረሰቦች ከፍተኛ በደል እየደረሰባቸው ነው ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑ እንደራሴዎች ተናገሩ፡፡ ለሚደርሰው በደል ዋነኛው ምክንያት የአካባቢው ነዋሪዎች በምርጫ ወቅት የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲን በመምረጣቸው ነው ብለዋል፡፡ ንጋቱ ሙሉ ሸገርን ወሬዎች፣ መ

በአፋርና በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት የወደሙ ት/ቤት መልሶ መገንቢያ እስካሁን 2.8 ቢሊየን ብር ተሰብስቧል ተባለ፡፡ በጦርነቱ ከ300 ት/ቤቶች በላይ ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ይታወሳል፡፡ ተመስገን አባተ ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

bottom of page