ታህሳስ 3፣ 2015- በጣሊያን ሮም በአንድ ካፌ ውስጥ በተከፈተ ተኩስ ሶስት ሴቶች መገደላቸው ተሰማ
- sheger1021fm
- Dec 12, 2022
- 1 min read
Updated: Dec 13, 2022

ታህሳስ 3፣ 2015
በጣሊያን ሮም በአንድ ካፌ ውስጥ በተከፈተ ተኩስ ሶስት ሴቶች መገደላቸው ተሰማ፡፡
የተገደሉት ሴቶች በመኖሪያ አካባቢ ምክክር ላይ ነበሩ ተብሏል፡፡
የነዋሪዎች ኮሚቴዎች ወኪሎች እንደነበሩ TBP በድረ ገፁ ፅፏል፡፡
በጥቃቱ ከተገደሉት ሌላ 4 ሰዎች ደግሞ አካላዊ ጉዳት ገጥሟቸዋል ተብሏል፡፡
የ57 አመቱ ጥቃት አድራሽ ከመኖሪያ አካባቢ ማህበር የቦርድ አባሎች ጋር ተወዛጋቢ ነበር መባሉ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡
ግለሰቡ ጥቃቱን ከፈፀመ በኋላ በፖሊስ ተይዞ መታሰሩ ታውቋል፡፡ በጥቃቱ ከተገደሉት መካከል አንደኛዋ የጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጓደኛ ነበረች ተብሏል፡፡
የኔነህ ከበደ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments