በኢትዮጵያዊያን ሐኪሞች የጋራ ባለሃብትነት የተቋቋመው የላንሴት ስፔሻላይዝድ የሕክምና ማዕከል ሰራተኞች በገና በዓል ዋዜማ ደም ሲለግሱ ውላዋል።
ሆስፒታሉ ባለፉት 3 ዓመታት ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡
አርብ ዕለትም የሆስፒታሉ ሰራተኞች እና ነዋሪዎች በደም እጦት ምክንያት እናቶች፣ አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች እና ሌሎች ደም የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች እንዳይጎዱ ደም ሲለግሱ ውለዋል፡፡
ከለጋሾች የሚገኝ ደም በሚያንስባቸው ጊዜያት ቀዶ ህክምና የሚፈልጉ የህክምና አገልግሎቶች በደም እጥረት ምክንያት የቀጠሮ ጊዜያቸው እንደሚራዘም ሲነገር ይሰማል።
ለዚህም የላንሴት ሰራተኞች ደም እንለግስ ሲሉም ጥሪ አቅረበዋል፡፡
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments