top of page

ታህሳስ 26፣2017 -ሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀጥ በታየባቸው አካባቢዎች ከሚኖሩ 80,000 ሰዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በመለየት ከአካባቢው በማራቅ ለማሥፈር እየሰራሁ ነው ሲል መንግስት ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Jan 4
  • 1 min read

ሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀጥ በታየባቸው አካባቢዎች ከሚኖሩ 80,000 ሰዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በመለየት ከአካባቢው በማራቅ ለማሥፈር እየሰራሁ ነው ሲል መንግስት ተናገረ፡፡


ሰሞኑን በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ በታየባቸው አካባቢዎች የጉዳቱን መጠን አሠሣ እያደረግኩ ነው ብሏል፡፡


በተለይ ለመሬት መንቀጥቀጡ ማዕከል የሆኑ 12 ቀበሌዎች እንደተለዩም ተጠቅሷል፡፡


በእነዚህ አካባቢዎች መንግሥት ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በቦታው በማሰማራት የጉዳቱን መጠን አሠሣ እያደረግኩ ነው ሲል መንግስት ተናግሯል፡፡

በአፋር፣ ኦሮሚያ እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ማዕከላቸውን አድርገው የተለያየ መጠን ያላቸው የርዕደ መሬት ክሥተቶች በተደጋጋሚ መከሠታቸው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መረጃ አስረድቷል፡፡


የመሬት መንቀጥቀጡ በማኅበራዊ አግልግሎት ሰጭ ተቋማት፣ በኢኮኖሚ ተቋማት እና በመሠረተ ልማት ላይ ሊኖረው የሚችለው ተጽዕኖ ላይ ክትትል እየተደረገ እንደሆነም ጠቁሟል፡፡


የመሬት መንቀጥቀጡ በዋና ዋና ከተሞች የጎላ ተጽዕኖ እስካሁን አላደረሰም ያለው አገልግሎቱ ህብረተሰቡ በባለሙያዎች የሚሰጡ የጥንቃቄ መልእክቶችን እንዲከታተልና በጥብቅ እንዲተገብርም አሳስቧል።


ጉዳዩን በቅርበት ተከታትዬ አስፈላጊ መረጃዎችን በሚመለከታቸው ተቋማት አማካይነት አደርሳልሁ ብሏል መንግስት፡፡


ሰሞኑን በተለይም በአፋር ክልል በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እያጋጠመ እንደሆነ በተለይም ትናንትና ሌሊት የተከሰተውና በሬክተር ስኬል 5.8 ሆኖ የተለካው ከፍተኛው መሆኑ ተዘግቧል።

コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page