ታህሳስ 25፣2017 - የአዲስ አበበ ቄራዎች ድርጅት ለገና በዓል ከ4,000 በላይ የእንሰሳት እርድ ለመከወን ተዘጋጅቻለሁ አለ
- sheger1021fm
- Jan 3
- 1 min read
የአዲስ አበበ ቄራዎች ድርጅት ለገና በዓል ከ4,000 በላይ የእንሰሳት እርድ ለመከወን ተዘጋጅቻለሁ አለ።
የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አታክልቲ ገብረሚካኤል ቅድመ ዝግጅታቸውን አስመልክቶ ዛሬ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች መግለጫ ሰጥተዋል።
በዚህም ወቀት ለበዓሉ ከ4,000 በላይ የቁም እንሰሳት ለማረድ ተዘጋጅተናል፤የሚያሳርዱት በአብዛኛው በከተማዋ ያሉ ልኳንዳ ቤቶች ናቸው ብለዋል።
ይሁንና ማንኛውም ግለሰብ ለበዓሉ የገዛቸውን የቁም እንሰሳት ወደ ቄራዎች ድርጅት ይዞ ቢመጣ የእንሰሳቱን ጤንነት በህክምና ባለመያዎች አረጋግጠን በተ ጣጣኝ ዋጋ የእርድ አገልግሎት እንሰጣለንም ብለዋል።
በዚህም መሰረት አንድ በሬ በ1470 ብር፣ በግና ፍየል ደግሞ በ165 እንደሚያርዱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ አንስተዋል።

በተጨማሪም ስጋን በኪሎ መግዛት ለሚፈልጉ ደምበኞቹ በተለምዶ ቄራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቅጥር ግቢው ዙሪያ ባሉ የስጋ መሸጫ ሱቆች የበግ ስጋ በኪሎ በ600 ብር፣ የፍየል በ620 ብር እና የበሬ ስጋ በኪሎ በ700 እንዳቀረበ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ባለፉት 6 ወራት ህገ ወጥ እርድንና የስጋ ዝውውር ለመቆጣጠር በተሰራ ሥራ 6 ሺህ 620 ኪሎ ግራም የተበከለ ስጋ እንደተወገደ አቶ አታክልቲ አስረድተዋል።
በዚህ ህገወጥ ተግባር ውስጥ ተሳትፈዋል የተባሉና ጤናማነቱ ያልተረጋገጠ ስጋን ለማህበረሰቡ ሲሸጡ የተደረሰባቸው 150 ልኳንዳ ቤቶች ላይ ከማሸግ እስከ ገንዘብ ቅጣት የደረሰ እርምጃ እንደተወሰደም ጠቅሰዋል።
ድርጅቱ በመደበኛነት ከበዓላት ውጭ ባሉት ቀናት በየቀኑ የ3ሺህ እንሰሳት እርድ እንደሚከውን ተናግሯል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5rs
Comments