top of page

ታህሳስ 25፣2017 - የአንድ ወር የደንበኞች አገልግሎት ወር ጀምሬያለሁ ሲል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Jan 3
  • 1 min read

ከደንበኞቼ ጋር ስለ አገልገሎት አሰጣጤ ምን ጎደለ፣ ምን ይሻሻል የምልበት፣ የላቀ አፈፃፀም ያሳዩትንም የምሸልምበት የአንድ ወር የደንበኞች አገልግሎት ወር ጀምሬያለሁ ሲል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተናገረ።


''የደንበኞች አግልግሎት ወሩ ለደንበኞች ምስጋና የሚሰጥበት እና ጥራት ያለው አገልገሎት የመስጠት ቃልም የሚታደስበት ነው'' ሲሉ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ተናግረዋል።


ለ 30 ቀናት የሚቆየው የባንኩ ደንበኞች የአገልግሎት ወር "የላቀ አገልግሎት ደስተኛ ደንበኛ" የሚል ርዕስ ተሰጥቶታል።


በአንድ ወር ቆይታውም በዋና መስሪያ ቤት እና በዲስትሪክቶች ደንበኛ የተመለከቱ ግኑኝነት ለማጥበቅ የሚያግዙ ዝግጅቶች ይካሄዳሉ፣ የላቀ አፈፃፀም ባሳዩ ቅርንጫፎችም ጉብኝት ይደረጋል ተብሏል።

አውደ ርዕይ፣ ደም ልገሳ፣ የስፖርት ጨዋታዎች ዝግጅቱን እንደሚያጅቡት ተነግሯል።


ባንኩ ከደንበኞቹ ጋር ያለውን የስራ ግኑኝነት ለማጥበቅ የደንበኞች አገልግሎት የጥራት  የአሰራር ስርዓት ሰነድ እያዘጋጀን መሆኑንም አስረድቷል።


በዛሬው ዕለት በዋናው መስሪያ ቤት በተዘጋጀው የደንበኞች አገልግሎት ወር ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩ እና የኢትዮጵያ ንግድ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አህመድ ሺዴ ተገኝተዋል።


የ82  ዓመቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞቼ ብዛት 45 ሚሊዮን፣ ጊዚያዊዎቹን ጨምሮ በአጠቃላይ  82,000 ሰራተኞች አሉኝ ብሏል።


81 በመቶ ደንበኞቼ በዲጂታል መላ ተጠቃሚ ሆነዋል ይህም ከአሰብኩት ቀድሞ የተሳካ እቅዴ ነው ሲል አስረድቷል።


የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 1.97  ትሪሊዮን ብር፣ ተቀማጩ 1 ትሪሊዮን 419 ቢሊዮን፣ ካፒታሉ ደግሞ 131 ቢሊዮን ብር ደረሷል ተብሏል።


ንጋቱ ሙሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page