top of page

ታህሳስ  25፣2016 - እየተገነባ ያለው የፎረንሲክ ምርመራ ማዕከል በቅርቡ ወደ ስራ ይገባል ተባለ፡፡

  • sheger1021fm
  • Jan 4, 2024
  • 1 min read

እየተገነባ ያለው የፎረንሲክ ምርመራ ማዕከል በቅርቡ ወደ ስራ ይገባል ተባለ፡፡

 

የፖሊስን ስነ ምግባር የሚሸረሽሩ ስራዎች ለማስተካከል እየተሰራ ነው ተባለ፡፡

 

ይህ የተባለው የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ 99 ኢንስፔክተሮችን በዋና ኢስፔክተርነት ባስመቀረበት ወቅት ነው፡፡

 

የተመረቁት ዋና ኢንስፔክተሮች በዘመናዊ መንገድ ወንጀል ምርመራ እና ሌሎች የተለያዩ ስልጠናዎች ወስደዋል ተብሏል፡፡

 


የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እንዳሉት ኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፖሊስ ኢንስቲትዩት እየገነባች ነው።

 

ይህም ለሀገሪቱ ፖሊስ እድገት ትልቅ በር ይከፍታል ብለዋል፡፡

 

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ የፌደራል ፖሊስ ወንጀልን ለመከላከል የሚረዳ መተግበሪያ እያለማ ነው ያሉ ሲሆን ህብረተሰቡ በቀላሉ በመተግበሪያ ከተቋሙ ጋር በመገናኘት ወንጀልን መከላከል ይችላል ብለዋል፡፡

 


ባለፉት ዓመታት የፖሊስ ስነ ምግባር የሚሸረሽር ስራዎች ተሰርተዋል የተባለ ሲሆን አሁን ላይ ፌደራል ፖሊስ ይህንን ለማስተካከል እየሰራ ነው ተብሏል።

 

የፌደራል ፖሊስ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን የሀገሪቱን ሰላም ለማስጠበቅ እየሰራ ነው መባሉንም ሰምተናል።

 



የመጀመሪያው የፖሊስ አዛዥ የብርጋዴር ጀነራል ፅጌ ዲቦ ሀውልትም በዚሁ ወቅት ተመርቋል፡፡


በረከት አካሉ

 

 

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

 

Comentarios


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page