በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮች ከቀናት በኋላ በነባሩም ሆነ አዳዲስ ውለታ የሚገቡትን ተበዳሪዎች የብድር ወለድ ምጣኔን ከ3 እስከ 5 በመቶ ከፍ ሊያደርጉ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ሸገር ሬዲዮ ከታማኝ የባንክ ምንጮቹ ሰምቷል፡፡
ይህም #የብድር_የወለድ ምጣኔው እስከ 20 እና 22 በመቶ ይደርሳል እንደማለት ነው፡፡
ከዓመታት በፊት የነበረውን የገንዘብ የመግዛት አቅም እና የኢኮኖሚውን ሁኔታ እንዲሁም የገቢ መጠናቸውን ታሳቢ በማድረግ ከባንክ በመበደር ከውጭ እቃ የሚያስመጡ ነጋዴዎች ሆኑ ቤት የገዙ ተበዳሪዎች በተበደሩት ወለድ ላይ ከ3 እስከ 5 በመቶ ጭማሪ ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡
አንድ ተበዳሪ ከዓመታት በፊት ከባንክ በ17 በመቶ ወለድ ተበድሮ ከነበረ በአሁኑ ወቅት ባንኮች ወለዱን 5 በመቶ በመጨመር 22 በመቶ ሊያደርሱት በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ምንጫችን ነግረውናል፡፡
በአሁኑ ወቅት ገበያው እራሱን እያረጋጋ ነበር ይሁንና ጥቂት ቁጥር ባላቸው #ባንኮች ምክንያት ተመልሶ ዋጋ ሊንር ነው የሚሉት ምንጫችን በተለይም ከውጭ እቃ ለማስገባት ከባንኮች ብድር አስቀድመው ውል ገብተው የተበደሩትም ሆኑ አዳዲስ ተበዳሪዎች ከፍተኛ በሆነው የብድር የወለድ ጭማሪ ምክንያት የሚስገቡት እቃ እጅግ ይንራል ይህም መልሶ ሸማቹ ላይ የሚወደቅ ይሆናል ብለዋል፡፡
አንድ ተበዳሪ ከባንክ ጋር የብድር ኮንትራት ሲገባ ባንኩ ወለድ እንዲጨምር ይሁንታውን ይሰጣል፡፡
ባንኮች ብድር ስለሚሰጡ እና በኮንትራቱ መሰረት የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ በመመልከት የወለድ ምጣኔውን እንዲጨምሩ ስምምነት ተደረገ ማለት ግን እንደፈለጉት ህግንም እንዲተላለፉም ሆነ ሀገርን ወደ አደገኛ የኢኮኖሚ ችግር የማስገባት መብት አላቸው ማለት አይደለም ተብሏል፡፡
አሁን ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከ1 በመቶ እስከ 2 በመቶ የብድር የወለድ ምጣኔን ሊያስጨምር የሚችል መሆኑን ማየት ይቻላል ይሁንና ከ3 - 5 በመቶ ግን በፍጹም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ሊሸከመው የሚችል ዓይነት አይደለም ሲሉ ምንጫችን ነግረውናል፡፡
የኔነህ ሲሳይ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
コメント