ታህሳስ 23፣2017 - ‘’75 በመቶው የተቋሙ ደንበኛ የ1፣ የ3 እና የ5 ብር ፓኬጅ የሚሞላ ነው’’ ኢትዮ ቴሌኮም
- sheger1021fm
- Jan 1
- 1 min read
ኢትዮ ቴሌኮም ተግባራዊ ያደረግሁት የታሪፍ ማሻሻያ 75 በመቶ ተጠቃሚዎችን የሚመለከት አይደለም አለ፡፡
ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬሕይወት ታምሩ በፓርላማው ተገኝተው ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ ለቀረቡ ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ 75 በመቶው የተቋሙ ደንበኛ የ1፣ የ3 እና የ5 ብር ፓኬጅ የሚሞላ ነው ብለዋል፡፡
የተጠቀሱትን የገንዘብ መጠን የሚጠቀሙት ላይም ምንም ዓይነት የታሪፍ ጭማሪ አልተደረገም ብለዋል፡፡
ባለፉት 6 ዓመታት ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው በአነስተኛ ታሪፍ እንደነበር ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል፡፡
ይሁንና የማክሮ ኦኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ለብዙዎች የማስፋፊያ ስራዎችን የምንገዛቸውን አገልግሎቶች ግዥ የምንፈፅመው በዶላር በመሆኑ ታሪፍ ለማሻሻል ተገደናል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments