በነበረው ግጭት ምክንያት 128 የጤና ተቋማት ሙሉ ብሙሉ እና በከፊል ወድመውብኛል ሲል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተናገረ፡፡
በክልሉ አሁን ሰላም ስለሰፈነ የወደሙ የጤና ተቋማትን በማቋቋሙ እርዱኝ ብሏል፡፡
ይህንን የነገሩን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አለም ደበሎ ናቸው፡፡
የደረሰው ጉዳት ተጠንቶ ለፌዴራል መንግስት ሪፖርት ተድርጓልም ብለውናል ሀላፊው፡፡
ነገር ግን በጤና ተቋማቱ የደረሰው ውድመት በመንግስት አቅም ብቻ መልሶ ለመገንባት የሚከብድ እንደሆነ አንስተዋል፡፡
ስለሆነም የቻለ ሁሉ በ #ህክምና_መሳሪያም ሆነ በሌላው ቢረዳን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በተለይ ከሁለት ዓመት በፊት የማንገባባቸው ወረዳዎች ነበሩ ሲሉ ተናግረዋል አቶ አለም፡፡
አሁን ግን ባለሞያዎች እየተመደቡ የጤና አገልግሎት በተለያዩ ቦታዎች እንደተጀመሩ ጠቅሰዋል፡፡

ለጤና ተቋማቱ ውድመት ምክንያት የነበረው #የጸጥታ_ችግር ተፈትቶ አሁን ላይ ሰላም ወርዷል ብለዋል፡፡
የቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለዓመታት በዘለቀ ግጭት ውስጥ እንደነበረ ይታወሳል፡፡
በዚህም የጤና፣ የትምህርት አገልግሎትን ጨምሮ የበዙ ማህበራዊ መስተጓጉሎች አጋጥመው እንደቆዩ ተነግሮ ነበረ፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የክልሉ መንግስት ጫካ ከነበሩ ታጣቂዎች ጋር ስምምነት ፈጥሬ ሰላም ወርዷል ብሏል፡፡
ከታጣቂዎቹ መካከልም በካቢኔነት ጭምር ሾሜም አብረን እየሰራን ነው ማለቱ ይታወሳል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ማንያዘዋል ጌታሁን ያዘጋጀውን በፋሲካ ሙሉወርቅ
Comments