top of page

ታህሳስ 23፣2017 - አዋጭ የተሰኘው የብደርና ቁጠባ ተቋም በንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ አባላቱ በነፃ የገና ባዛር አሰናድቷል

አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር በንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ አባላቱ በነፃ የገና ባዛር አሰናድቷል፡፡


ከተቋሙ ብድር ወስደው የተለያየ ምርት እያመረቱ ያሉ ከ70 በላይ ለሆኑ አባላቱ በአዲስ አበባ መገናኛ አካባቢ ሾላ የገበያ ማዕከል ውስጥ ባዛር አሰናድቷል፡፡


አዋጭ ቁጠባን ከአባላቱ በማሰባሰብ ለ42,000 አባላቱ ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ሰጥቶ እያንቀሳቀሰ እንደሆነ የተናገሩት የህብረት ስራ ማህበሩ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ዘሪሁን ሸለመ ናቸው፡፡

ይህ ባዛር አዋጭ ለአባላቱ ብድር መስጠት ብቻ ሳይሆን የተሰጠው ብድር ከምን እንደደረሰ ማሳያ ነው ያሉት ደግሞ የአዋጭ የስራ አመራር ቦርድ ዋና ስብሰባ አቶ መስፍን ገብረስላሴ ናቸው፡፡


ከታህሳስ 22 እስከ ታህሳስ 28 2017 ዓ.ም በሚቆየው የገና ባዛር ተሳታፊ አባላት የራሳቸው ምርት እንዲሁም ሌሎች ግብአቶችን ይዘው በመቅረብ ለሸማቾች ምቹ ገበያን ይፈጥራሉ ተብሏል፡፡


በባዛሩ ላይ የሀገር ባህል ልብሶች፣ የቤት እቃዎች፣ የቆዳ ውጤቶችና የመሳሰሉት ይገኙበታል ተብሏል፡፡



ማርታ በቀለ

Comments


bottom of page