በኢትዮዽያ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ በተመለከተ ደረቅ ቆሻሻ በአካባቢ ሥነ-ምህዳር እና በሰዎች ደኅንነትና ጤና ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መሆኑ ተነግሯል።
ይህንን በተመለከተም #ደረቅ_ቆሻሻ በአካባቢ እና በሰዎች ደህንነትና ጤና ላይ እያስከተለ ያለውን ተፅእኖ እና ጉዳት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይበጃል የተባለ ረቂቅ ሰነድ ተሰናድቷል።
ውጤታማ የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ፣ አጓጓዝ፣ አከመቻቸት፣ መልሶ መጠቀም፣ መልሶ ኡደት እና አወጋገድ ሥርዓት እንዴት ይዘርጋ የሚለው እረቂቅ አዋጁ የፕላስቲክ አምራቾችን ስጋት ላይ ጥሏል።
በዚህ ጉዳይ የኢትዮዽያ ጎማና ፕላስቲክ ማህበር ረቂቁ ግልፅ እንዳልሆነ ነግሮናል።
የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ምንተስኖት ለማ ዘርፉ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚፈልግ መሆኑን አንስተው፤ እንደውም #የፕላስቲክ_አምራቾች አካባቢን ያፀዳሉ እንጂ አካባቢን አይበክሉም ሲሉ ይሞግታሉ።
የፕላስቲክ አምራቾች ለብዙ ሰው እንጀራ በመፍጠር በኢንቨስትመንቱ በስፋት የሚሳተፉ በመሆኑ፤ እንዲሁም ፕላስቲክ ያልገባበት ቦታ አለመኖሩን በመገንዘብ እንዴት አካባቢ ይጠበቅ? በምንስ ይተካ በሚለው ጉዳይ ጥንቃቄና ምክክር እንደሚያስፈልግ ነግረውናል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ተሁቦ ንጉሴ
በፕላስቲክ ምርት ዙሪያ የቀረበው ረቂቅ ህግን የተመለከተ ዘገባን ለማንበብ…. https://tinyurl.com/3tnss367
Comentarios