top of page

ታህሳስ 22፣2017 - ''በትግራይ ክልል ባሉ ከተሞች ከቲባውን አገናኙኝ ብዬ ወደ ቢሮ ስልክ ስደውል “የትኛውን ከንቲባ“ ተብዬ እየጠየቃለሁ'' እንባ ጠባቂ ተቋም

  • sheger1021fm
  • Dec 31, 2024
  • 1 min read

 ''ከንቲባውን አገናኙኝ ብዬ ወደ ቢሮ ስልክ ስደውል 'የትኛውን ከንቲባ' ተብዬ እጠየቃለሁ'' ሲል የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡


''በሕወሃት ፓርቲ መካከል በተፈጠረው ልዩነት ምክንያት ህዝቡ እየተንገላታ ነው'' ሲል የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የመቀሌ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ተናግሯል፡፡


በሕወሃት መካከል የተፈጠረው መከፋፈል ከተሞች ሁለት ከንቲባ እና አስተዳደሪ እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡


ይህም ተገልጋዩ ለእንግልት ዳርጓል ብሏል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ፡፡


የክልሉ ዋና ከተማ መቀሌ እና አዲግራትን ጨምሮ በክልሉ ያሉ አንዳንድ ወረዳዎች በጊዜአዊ አስተዳደሩም እና በእነ  ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል(ዶ/ር) በሚመራው ህወሃትም ከንቲባ እና አስተዳዳሪ ይሾምላቸዋል ሲሉ የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ፀሃዬ አንባዬ አስታውሰዋል፡፡


ይህም አንዱ ለአንዱ ስለማይታዘዝ ተገልጋዩ ጉዳዩን የሚፈጽምለት አጥቶ ተቸግሮ ነው ያለው ሲሉ አቶ ጸሃዬ እንባዬ አስረድተዋል፡፡


በተመሳሳይ ወረዳ እና ከፍለ ከተማ ላይ ያሉ የስራ ሃላፊዎች  አንዱ የመራውን ደብዳቤ ሌላኛው እኔ የእገሌን ትዕዛዝ አልፈጽምም ይላሉ ሲሉ አቶ ጸሃዬ ተናግረዋል፡፡


በሌላ በኩል የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ራሱ የህዝብን አቤቱታ ለማስፈፀም መቸገሩን ነገሮናል፡፡


በሕወሃት መካከል የተፈጠረው ልዩነት ከንቲባውን ፈልገን ስልክ ስንደውል እንኳን 'የትኛውን ከንቲባ' እየተባልን እየተጠየቅን ጉዳይ ለማስፈፀም ተቸግረናል ብሏል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…


ያሬድ እንዳሻው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page