ታህሳስ 21፣2017 - የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት በ100 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
- sheger1021fm
- Dec 30, 2024
- 1 min read
የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጂሚ ካርተር በ100 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ካርተር የአሜሪካ 39ኛ ፕሬዚዳንት ነበሩ ።
ጂሚ ካርተር በ100 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን በስማቸው የሚጠራው የካርተር ማዕከል ማርዳቱን BBC ፅፏል።

ካርተር የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ከመሆናቸው አስቀድሞ የጆርጂያ ግዛት አስተዳዳሪ እንደነበሩ መረጃው አስታውሷል።
ጂሚ ካርተር ከየትኛውም የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ረጅም ዕድሜ የኖሩ ናቸው ተብሏል።
ምንነቱ በውል ባልተጠቀሰ የጤና እክል ታማሚ ሆነው መቆየታቸው ተጠቅሷል።
የአስተዳደር ዘመናቸው በምጣኔ ሐብታዊ እና በዲፕሎማቲክ ቀውሶች የተሞላ እንደነበር መረጃው አስታውሷል።
ከፕሬዚዳንትታቸው ብኋላ በሰላምና በሰብዓዊ ተግባራት ባከናወኗቸው ተግባራት ለኖቤል የሰላም ሽልማት መብቃታቸውን በዘገባው ለትውስታ ተጠቅሷል።
Comments