top of page

ታህሳስ 21፣2017 - 70 የሚደርሱ የሀገር ውስጥ አምራቾች የተሳተፉበት ኤግዚቢሽን ዛሬ ተከፈተ

  • sheger1021fm
  • Dec 30, 2024
  • 1 min read

70 የሚደርሱ የሀገር ውስጥ አምራቾች የተሳተፉበትና ከታህሳስ 18 እስከ 27፣2017 ዓ.ም የሚቆይ ኤግዚቢሽን ዛሬ ተከፈተ፡፡


የኤግዚቢሽኑ ተሳታፊዎች ምርቶቻቸውን ይዘው የቀረቡት ካሳለፍነው ዓርብ ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ቢሆንም፤ መክፈቻው ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 21 ቀን ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ፍል ውሃ አካባቢ በሚገኘው አዲስ አውትሌት ሴንተር ተከናውኗል፡፡


’’የእኛ ምርት ለእኛ’’ በሚል መሪ ቃል በተሰናዳው ኤግዚቢሽን ከመላው የሀገሪቱ ክፍሎች የተጋበዙ በጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ በቆዳ ውጤቶች፣ በምግብና መጠጥ ማቀነባበር፣ በኬሚካል፣ በእንጨትና ብረታብረት ውጤቶች ምርት ላይ የተሰማሩ አምራቾች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በስነስርዓቱ ላይ ያገኘናቸው የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና የገበያ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚው አቶ ስዩም ሁጅራ ተቋማቸው የኤግዚቢሽኑ 70 በመቶ ወጪ በመሸፈን የአምራቾቹን ገበያ ለማስፋት እንደተሰናዳ ነግረውናል፡፡


በሀገር ውስጥ የተሰሩ ምርቶች ብቻ የቀረቡበት ኤግዚቢሽኑ እስከ ገና በዓል ዋዜማ ታህሳስ 27 ቀን 2017ዓ.ም እንደሚቆይ ሰምተናል፡፡


ምንታምር ፀጋው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page