ታህሳስ 21፣2017 ''ካሉ አካል ጉዳተኛ ህፃናት ውስጥ ከ85 እስከ 90 በመቶ የሚሆኑት የትምህርት እድል እያገኙ አይደለም'' ኢሰመኮ
- sheger1021fm
- Dec 30, 2024
- 1 min read
በኢትዮጵያ ካሉ አካል ጉዳተኛ ህፃናት ውስጥ ከ85 እስከ 90 በመቶ የሚሆኑት የትምህርት እድል እያገኙ አይደለም ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ፡፡
ለአካል ጉዳተኞች የመማሪያ ቦታ፣ መምህር የለንም በሚል ትምህርት ቤቶች አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች አይቀበሉም ተብሏል፡፡
የኢሰመኮ የሴቶች፣ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ ወላጆች አካል ጉዳተኛ ሕፃናትን ወደ ትምህርት ቤት ሊያስመዘግቡ ሲሄዱ የግልም ሆነ የመንግስት ትምህርት ቤቶች አንቀበልም ብለው እንደሚመልሷቸው በተለያዩ ጊዜያቶች ወላጆች አቤቱታቸው ለኮሚሽኑ እንደሚያቀርቡ ነግረውናል፡፡
ኮሚሽኑም በጉዳዩ ላይ ትምህርት ቤቶችን ሲጠይቅ የአቅም ችግር አለብን ይላሉ ያሉት ኮሚሽነር ርግበ በትምህርት ቤቶች በኩል የሚሰጠው ምክንያት አሳማኝ አይደለም፣ እንዲያርሙም እየጠየቅን ነው ብለዋል።
በቤተሰብ እና በራሳቸው ጥራት ተምረው ወደ ስራው አለም የተቀላቀሉ አካል ጉዳተኞች እንደማንኛውም ዜጋ ታክስ የሚከፍሉ ቢሆንም በአገልግሎት እኩል ተጠቃሚ አለመሆናቸውን ኮሚሽነር ርግበ ተናግረዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ፍቅሩ አምባቸው
Comments