top of page

ታህሳስ 20፣2016 -የፀጥታ ችግርን ሲመሩ እና ሲያስተባብሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው በህግ እንዲታይ እየተሰራው ነው ሲል መንግስት ተናገረ

በአማራ ክልል በተከሰተው የፀጥታ ችግር መፈጠር መነሻ የሆኑ፣ ግጭቱን ሲመሩ እና ሲያስተባብሩ የነበሩ 360 ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው በህግ እንዲታይ እየተሰራው ነው ሲል መንግስት ተናገረ፡፡


288 ሰዎች ደግሞ ጉዳያቸው በ’ደረቅ ወንጀል’ የሚታይ ናቸው ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በሰጠው መግለጫ ጠቅሷል፡፡


በክልሉ አብዛኛው አካባቢም አንፃር ሰላም ሰፍኗል ሲሉ የአገልግሎቱ ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ ተናግረዋል፡፡


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comentarios


bottom of page