top of page

ታህሳስ 2፣2016 - ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከግብር በፊት ከ836 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ አገኘሁ አለ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በ2015 የበጀት ዓመት ከግብር በፊት ከ836 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ አገኘሁ አለ።


ትርፉን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ88 በመቶ ብልጫ አለው ተብሏል።

 

ባንኩ ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰብስቤያለሁ  ያለ ሲሆን ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ46 በመቶ እድገት አሳይቷል ብሏል።

 

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለባለ አክሲዮኖች የሚከፍለው የትርፍ ድርሻ ወደ 29.2 በመቶ ከፍ አድርጓል ያሉት የባንኩ የስትራቴጂ እና ትራንስፎርሜሽን ረዳት ቺፍ ወይዘሮ መዓዛ ወንድሙ ካለፈው ዓመት የትርፍ ድርሻ ክፍፍሉ 18.1 በመቶ ብልጫ አሳይቷል ተብሏል።

 

የባንኩ ጠቅላላ ሀብት 19 ቢሊዮን ደርሷል የተባለ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ34 በመቶ ብልጫ ታይቶበታል ብለዋል ወይዘሮ መአዛ ወንድሙ።

 

የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብም 14.3 ቢሊየን መሆኑን የተናገሩት ወይዘሮ መዓዛ የ30 በመቶ እድገት አሳይቷል ብለዋል።

የባንኩ አጠቃላይ የደንበኛ ብዛት 1.2 ሚሊየን መድረሱን የተናገሩት ደግሞ የባንኩ የማርኬቲንግ እና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ፍቃዱ ይህም አምና ከነበረበት የ75 በመቶ እድገት አሳይቷል ሲሉ አስረድተዋል ።

 

በበጀት አመቱ የባንኩ ቅርንጫፍ 152 ደርሷል የተባለ ሲሆን በበጀት አመቱ ማብቂያ 230 ቅርንጫፎች ለማድረስ እየሰራን ነው ሲሉ አቶ ቢኒያም ተናግረዋል።

 

የባንኩ  የተከፈለ ካፒታል 2.1 ቢሊዮን ብር፣ የባለ አክሲዮኖች ብዛትም 20ሺ መድረሳቸውን ሰምተናል።

 

 

ፋሲካ ሙሉወርቅ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz



 

Comments


bottom of page