በኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል የማስፋፊያ ግንባታ ምክንያት ቤታችሁ ይፈርሳል የተባሉ ነዋሪዎች ‘’ለምንነሳበት ቤት ምትክ ተከልክለናል’’ ሲሉ ተናገሩ፡፡
‘’አልሚ ድርጅቱ ለኛ ሲል የገነባልንን ቤት ክፍለ ከተማው ከልክሎናል’’ ይላሉ፡፡
ክፍለ ከተማው በበኩሉ ‘’በህጋዊ መንገድ ከኔ ጋር ውል ለነበራቸው ሰዎች ምትክ ቤት ሰጥቻለሁ አሁን ቅሬታ ያቀረቡት ግን ከኔ ጋር ውል ከገቡ ወላጆቻቸው ቤት ቀጥለው ሰርተው ሲኖሩ የነበሩ ሰነድ አልባዎች ናቸው’’ ብሏል፡፡
#ኢትዮ_ጠቢብ_ሆስፒታል በበኩሉ ‘’የመኖሪያ ግንባታውን የገነባሁት ለሰነድ አልባ ነዋሪዎች ጭምር ነው’’ ብሏል፡፡
ነዋሪዎቹ እንዳሉት ያሉበት ቤት ‘’ሰነድ አልባ ቢሆንም የአየር ካርታ አለው ሆስፒታሉ ለልማት ተነሺዎች በሚል ቤቶችን ገንብቶልናል ክፍለ ከተማው ግን ይህንን ቤት እንዳናገኝ እያደረገን ነው’’ ብለዋል፡፡
ከ #ልማት_ተነሺዎች መካከል ለ4ቱ ብቻ ቤት ተሰጥቷል፡፡ 11 ለምንሆነው ግን ተከልክለናል በማለት ቅሬታቸውን ነግረውናል፡፡
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በበኩሉ ‘’መንግስት የሚያውቃቸው የቅሬታ አቅራቢ ወላጆችን እንጂ እነሱን አይደለም’’ ሲሉ የክፍለከተማው ቤቶች አስተዳደር ኃላፊ አቶ ጥላሁን ድሪባ መልሰዋል፡፡
የኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል የአስተዳደር ኃላፊ አቶ ሀይደር ናስር ‘’ተቋሙ የገነባው ቤት በልማቱ ለሚነሱ #ሰነድ_አልባ ናቸው ለተባሉት ነዋሪዎች ጭምር ነው’’ ሲሉ ነግረውናል፡፡
‘’ሆስፒታሉ ሰነድ አልባ ነዋሪዎች እንደነበሩ ያውቃል ምትክ ቤቱ ሲገነባም እነሱን ታሳቢ አድርገን ነው የገነባነው ‘’ ብለዋል፡፡
‘’ነዋሪዎቹም ለኛ የተገነባውን ቤት ክፍለ ከተማው ለሌሎች ሊሰጥ ተሰናድቷል ይህም ትክክል አይደለም ሆስፒታሉ ለኛ የገነባው በመሆኑ የሚገባው ለኛ ነው’’ ሲሉ ሞግተዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Kommentare