ምንም ረዳት የሌላቸውን 570 የአዕምሮ ህሙማንን የሚንከባከበው ጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል ለህሙማኑ ብዬ መገንባት የጀመርኩት ማዕከል በድጋፍ ማነስ ምክንያት ግንባታውን ለማቆም እየተገደድኩ ነው አለ፡፡
ማዕከሉ እንጦጦ ቁስቋም 17 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተከራይቶ በሚገኘው ቦታ 360 ወንዶች እና 210 ሴት አዕምሮ ህሙማንን እየተንከባከበ ይገኛል፡፡
ማዕከሉ ከኪራይ ወጪ እንዲድን ለታማሚዎቹም የተሻለ እንክብካቤ የሚያገኙበት ማዕከል ለመገንባት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 3,000 ካሬ ሜትር ቦታ መረከቡን የማዕከሉ መስራች አቶ መለስ አየለ ለሸገር ነግረዋል፡፡
Comments