top of page

ታህሳስ 18፣ 2015- በስፔን አንድ አውቶብስ ድልድይ ጥሶ ወንዝ ውስጥ በመውደቁ ሰባት ሰዎች መሞታቸው ተሰማ


በስፔን አንድ አውቶብስ ድልድይ ጥሶ ወንዝ ውስጥ በመውደቁ ሰባት ሰዎች መሞታቸው ተሰማ፡፡


አደጋው የደረሰው በሰሜናዊው ጋሊሲያ ግዛት እንደሆነ TVP ፅፏል፡፡


አውቶብሱ ድልድዩን ጥሶ የ30 ሜትር ያህል ጥልቀት ካለው ወንዝ ውስጥ መውደቁ ታውቋል፡፡


ባለስልጣናት አደጋው ምናልባትም በመጥፎ የአየር ሁኔታ ሳቢያ ሳይደርስ እንዳልቀረ ግምታቸውን ተናግረዋል፡፡


ብዙዎቹ መንገደኞች በሕይወት መትረፋቸው ታውቋል፡፡


አደጋው የገጠማቸው አብዛኞቹ የታሰሩ ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ ሲጓዙ የነበሩ ናቸው ተብሏል፡፡


የኔነህ ከበደ

ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

bottom of page