ታህሳስ 18፣ 2015- መንግስት ለነዳጅ የሚያደርገውን ድጎማ በሂደት ለማቆም ያሳለፈው ውሳኔ ወጪ እየቀነሰለትና የተከማቸበትንም ዕዳ እንዲያቃልል እያገዘው
- sheger1021fm
- Dec 27, 2022
- 1 min read
መንግስት ለነዳጅ የሚያደርገውን ድጎማ በሂደት ለማቆም ያሳለፈው ውሳኔ ወጪ እየቀነሰለትና የተከማቸበትንም ዕዳ እንዲያቃልል እያገዘው ስለመሆኑ ተነግሯል።
ውሳኔው ከነዳጅ ታክስ መንግስት ወደ ሃያ አንድ ቢሊየን ብር በሶስት ወር ጊዜ ብቻ እንዲሰበስብ አስችሏልም ተብሏል።
ይህ ታክስ ቀደም ሲል ሳይሰበሰብ ይቅር እንደነበር የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ተናግሯል።
ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ደግሞ ነዳጅ በድጎማ የሚገዙ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችን በታሪፉ መሰረት እንዲሰሩ የመቆጣጠር ግዴታ አለባቸው ተብሏል።
ንጋቱ ረጋሳ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments