
በአሜሪካ የበረዶ አውሎ ነፋስ እና ከባድ ቅዝቃዜ የገደላቸው ሰዎች ብዛት 56 መድረሱ ተሰማ፡፡
በአገሪቱ በመድረስ ላይ የሚገኘው የበረዶ አውሎ ነፋስ ከምንግዜውም የከፋ እንደሆነ ኒውስ ማክስ ፅፏል፡፡
የበረዶ አውሎ ነፋሱ ከካናዳ እስከ ሜክሲኮ ወሰን ያለውን ስፍራ ማካለሉ ተሰምቷል፡፡
መጥፎው የአየር ሁኔታና በረዷማው አውሎ ነፋስ በኒው ዮርክ ግዛት ብቻ 28 ሰዎችን መግደሉ ተሰምቷል፡፡
የወረደው የበረዶ ክምር ከምድር ከ1 ሜትር በላይ ከፍታ መድረሱ ታውቋል፡፡
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መጥፎ የአየር ሁኔታ ከፍተኛ ጉዳት ላደረሰበት ኒውዮርክ ግዛት የአጣዳፊ ድጋፍ ማፅደቃቸው ተሰምቷል፡:
የአደጋው ተጎጂዎች ብዛት ሊጨምር እንደሚችል ተሰግቷል፡፡
የኔነህ ከበደ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments