top of page

ታህሳስ 17፣2017 - በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል እየተካረረ የነበረውን ውጥረት የአንካራው ስምምነት እንዳረገበው ተነግሯል፡፡

በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል እየተካረረ የነበረውን ውጥረት የአንካራው ስምምነት እንዳረገበው ተነግሯል፡፡


ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ሶማሊያ የግዛቴ አካል ናት ከምትላት ሶማሌላንድ ጋር ያሰረችው ውል ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር ለገባችው የዲፕሎማሲ ውጥረት ምክንያት እንደሆነ ይታወሳል፡፡


በቱርክ መንግስት አንካራ ላይ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ መንግስታት ውጥረቱን ለማርገብ ችግራቸውንም በንግግር ለመፍታት ተግባብተናል ካሉ ቀናቶች ተቆጥረዋል፡፡


ለመሆኑ ከአንካራው ስምምነት በፊት ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ያሰረችው ውል ከዚህ በኋላ እድሉ ምን ይሆን?


የአፍሪካ ጉዳዮች እና የውጪ ግንኙነት ፖሊሲ ተመራማሪ ወርቁ ያዕቆብ (ዶ/ር) የአንካራው ስምምነት ለቀጠናው እፎይታን የሰጠ ቢሆንም ለኢትዮጵያ ግን ትልቅ የዲፕሎማሲ የቤት ስራ ጥሎ ማለፉን ያስረዳሉ፡፡


አንካራ ላይ ስለተደረገው ስምምነት በግልፅ እና በዝርዝር እስካሁን የተባለ ነገር ባይኖርም በወጣው መግለጫ ላይ ግን በሶማሊያ የሰፈረው የግብፅ ጦር ጉዳይ አንዱ መሆን ነበረበት ብለዋል ተመራማሪው፡፡


የግብፅ ጦር ለኢትዮጵያ በቀጠናው መስፈር የደህንነት ስጋት ስለሆነ ይህም ወደፊት በሚደረጉት ግንኙነቶች ላይ ትኩረት የሚሻው ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡


የግብፅ ሰላም አስከባሪ ወታደር በሶማሊያ እንዳይሰፍር ኢትዮጵያ ብርቱ የዲፕሎማሲ ትግል ማድረግ ከስምምነቱ በኋላ የሚጠበቅባት ትልቅ የቤት ስራ ነው ተብሏል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….



ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comentarios


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page