የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንሲስ ዓለማችን ሰላም እርቧታል አሉ፡፡
ዓለማችን ሰላምን ተርባለች ያሉት የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት እንደሆነ ዘ ኢንዲፔንደንት ፅፏል፡፡
ትርጉም አልባ ሲሉ የጠሩትም የዩክሬይኑ ጦርነት እንዲቆም ጠይቀዋል አባ ፍራንሲስ፡፡
ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መልዕክት አብዛኛው ክፍል የዩክሬይኑን ጦርነት የተመለከተ ነው ተብሏል፡፡
አባ ፍራንሲስ በአለም ዙሪያ ግጭት በሚስተዋልባቸው ቦታዎች የሚንገላቱ እና በብዙ የተቸገሩ ሰዎችንም እንዳሰቧቸው በዘገባው ተጠቅሷል፡፡
በአለም ዙሪያ ግጭት እና ጦርነት እንዲያበቃ መማፀናቸው ተሰምቷል፡፡
የኔነህ ከበደ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments