top of page
  • sheger1021fm

ታህሳስ 17፣ 2015- በአሜሪካ በከባዱ የክረምት ቅዝቃዜ ምክንያት የ38 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ


በአሜሪካ በከባዱ የክረምት ቅዝቃዜ ምክንያት የ38 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ፡፡


በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ እና ካናዳ ከባድ ቅዝቃዜ መከሰቱን ዘ ግሎብ ኤንድ ሜይል ፅፏል፡፡


በዚሁ መጥፎ የአየር ሁኔታ ምክንያት በካናዳም 4 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል፡፡


ቅዝቃዜው በበረዷማ ውሽንፍር የታጀበ ነው ተብሏል፡፡


በዚሁ መጥፎ የአየር ሁኔታ ምክንያት በአሜሪካ በሺህዎች የሚቆጠሩ የአውሮፕላን በረራዎች መሰረዛቸው ታውቋል፡፡


በአሜሪካም ሆነ በካናዳ የኤሌክትሪክ መጥፋት ያስከተለባቸው ቦታዎች እንዳሉ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

Recent Posts

See All
bottom of page