ላለፉት ዓመታት እድሜያቸው 14 ዓመት ለሆኑ ልጃገረዶች ሲሰጥ የነበረው የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት በዚህ ዓመት ከ 9 ዓመት ጀምሮ ላሉ ልጃገረዶች ሊሰጥ መሆኑ ተነገረ፡፡
የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በከተማዋ ከመጪው ሳምንት ጀምሮ የማህፀን ካንሰር መከላከያ ክትባቱን በትምህርት ቤቶች፣ ጤና ተቋማትና በጊዜያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች ይሰጣል ብሏል፡፡
ቢሮ የክትባት ዘመቻውን አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጠኞችን ጠርቶ ሲናገር እንደሰማነው እድሜያቸው ከ15 ዓመት በላይ ከሆኑ ሴቶች አምስቱ ለማህጸን በር ካንሰር ተጋላጭ መሆናቸውን ተናግሯል፤ ለዚህም የመከላከያ ክትባቱን መስጠት ተጋላጭነትን ለመቀነስ መፍትሄ መሆኑን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሃላፊው ዮሃንስ ጫላ(ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
ከ #ጡት_ካንሰር ቀጥሎ ለህብረተሰቡ ከፍተኛ የጤና ጋት የሆነውን የማህፀንበር ካንሰር በገዳይነቱ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በሽታው በዋናነት የሚከሰተው ሂውማንፓፒሎማ በተባለና በግብረ ስጋ ግንኙነት በሚተላለፍ ቫይረስ ነው ብለዋል፡፡
በተገላጭነት ደረጃ 15 ዓመት በላይ ከሆኑ ሴቶች ከአምስቱ ውስጥ 4ቱ ለዚህ ቫይረስ ተጋላጭ መሆናቸውንና ካንሰር በሽታን ከምንከላከልባቸው የተለያዩ ስልቶች አንዱ ታዳጊ ሴት ልጆችን በትምህርት ቤት እና ከትምህርት ቤት ውጪ ክትባት እንዲያገኙ ማድረግ ነው ሲሉ ዶ/ዮሐንስ ተናግረዋል፡፡
ላለፉት 5 ዓመታት #የማህፀን_በር_ካንሰር_መከላከያ ክትባቱ ሲሰጥ የነበረው እድሜያቸው 14 አመት ለሆኑ ታዳጊዎች ብቻ እንደነበርና አሁን በቂ የክትባት መጠን ስላለ እንዲሁም ቀድሞ ታዳጊዎች ክትባቱን ቢወስዱ ውጤታማነቱ ከፍ ያለ በመሆኑ ከዘጠኝ አመት ጀምሮ ላሉ ልጃገረዶች ይሰጣል ተብሏል፡፡
ክትባቱን ከመጪው ሳምንት ታህሳስ 21 እስከ 25፣2017 ዓ.ም ድረስ በከተማ ደረጃ ለመስጠት እንደታሰበ እና ከትምህርት ቤት ውጭ ያሉ ኑሯቸውን በጎዳና ያደረጉ ታዳጊዎችንም እንደሚያካትት ኃላፊው ጠቅሰዋል፡፡
90 በመቶ የሚሆኑ ልጃገረዶች በትምህርት ቤቶች ላይ የሚገኙ በመሆኑ በተለይ በሁሉም #የትምህርት_ተቋማት ላይ የሚገኙ መምህራንና ባለሙያዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ የተናገሩት ደግሞ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሀላፊው ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ናቸው፡፡
በኢትዮጵያ ከጡት ካንሰር በመቀጠል ሁለተኛ ገዳይ በሽታ የሆነው የማህጸን በር ካንሰር በየዓመቱ 7 ሺህ ያህል ሴቶች ሲያዙ 5,000 ያህሉ ህይወታቸውን እንደሚያጡ ሰምተናል፡፡
ምህረት ስዩም
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
コメント